Tuesday, November 20, 2012

በአፋር ክልል የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከትውልድ ወደ ትውልድ ለዘመናት ይዘውት የመጡትን እምነት በኢህአደግ ስርዓት በሚደገፉ ከሊባኖስ በመጡ የእስልምና ሃይማኖት ሰባኪዎች አስተምህሮ እንዲቀይሩ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣


www.demhit on line.com



    በደረሰን ዘገባ መሰረት በክልሉ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ያላመኑበትንና ያልተቀበሉትን ‘አሕባሽ’ የተባለ አዲስ እምነት በመላ ሃገሪቱ የሃይማኖት ነጻነት እንዲከበር በመጠየቅ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ከሚገኙ የሙስሊም ማህበረሰብ ጋር በመሆን ተቃውማቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል፣ ይህ በእንዲህ እያለ በክልሉ ዳጋን በተባለ ከተማ በእስር ላይ የሚገኙትን የሃይማኖት መሪዎችንና አስተባባሪ ኮሞቴን ይፈትሉን ለማለት ወደ ፖሊስ ጣብያ ያመሩ የሙስሊም ማህበረሰብ ከስርዓቱ ፖሊስ አባላት በተተኮሰባቸው ጥይት 7 ንጹሃን ዜጎች ሲገደሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሌሎች ደግሞ እንደታሰሩ ለማወቅ ተችለዋል፣
   የኢህአደግ መንግስት መብታችን ይከበር ብለው በጠየቁ የእስልምን ማህበረሰብ ላይ እየፈጸመው ያለውን ግፍ አቁሞ ህዝብ የመረጣቸው የሃይማኖት መሪዎችና አስተባባሪዎች እስኪፈቱ ድረስ አሕባሽን በመቃወም የሚያደርጉትን ተቃውሞ አጠናክረው እንደሚቀጡልበት አስምረውበታል፣
    ይህ በእንዲህ እያለ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች መልካም አስተዳደር ባለመኖሩና በበጀት እጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ማቆማቸውን ታውቋል፣
በዩኒቨርሲቲው በተከሰተው ችግር ምክንያት አንዳንዶቹ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው የኢህአደግን ስርዓት በመቃወም በትጥቅ ትግል በመፍለም ላይ ከሚገኙት ድርጅቶች ጋር የተቀላቀሉ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ እግራቸው ወደ መራቸው በመሰደድ ላይ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል፣