ባለፈው ህዳር 24 በዓለም ደረጃ ለ24ተኛ ግዜ። በአገር ደረጃ ደግሞ ለ23ኛ ግዜ። ‘ማካተት
ወሳኝ ነው’ በሚል መሪ ቃል የአካል ጉዳተኞች ቀን በአል ተከብሮ
ነበር፣ የአካል ጉዳተኞች ቀን ለ24ተኛ ጊዜ ተብሎ ሲከበር። በአካል ጉዳተኞች አያያዝ ያለው ስርአትና አመለካከት ለማየት
ስንሞክር ግን በተለይ በአገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ዝቅ
ብሎ የወረደ ነው፣
አካል ጉዳተኛ ስንል በተለያዩ ምክንያቶች ማለት በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ
አደጋ ኣካሉ ለጎደለ ሰዉ ሁሉም በእኩል ያካተተ ነው፣ አገራችን ኢትዮጵያም ኣካል ጉዳተኞች
በብዛት ካላቸው አገሮች ተጠቃሽ ናት፣ ምክንያቱም ከጥንት ጀምሮ ለዚች አገር በአገራዊ ፍቅር ስሜት የተነሳ ብዙ ጀግኖች አካላቸው ጎድለዋል፣
በዚህ መሰረት ደግሞ አገራችን ኢትዮጵያ ከማንኛዉም የባእድ አገዛዝ ነፃ
በመሆን ሉአላዊነትዋን አስከብራ ቆይታለች፣ ያለፉት ጨቋኝ የአገራችን ስርአቶች ለመጣል በተደረገው ትግልም
ቢሆ። ከ100 ሺ በላይ የሚሆኑ ጀግኖች ለአካል ጉዳተኝነት
ተዳርጓል፣ በተለይ ትግራይ ክልልን ወስደን ስንመለከታት እንኳ ካለፈው የትጥቅ ትግል በተያያዘ በብዛት ኣካል ጉዳተኞች ይገኙባታል።
ይህ ተከብሮ ያለፈው በአልም ለጦር ጉዳተኞች ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ለሁሉም
በተለያዩ ምክንያቶች አካላቸውን ያጡ የሚመለከትና በአለም ደረጃ የሚከበር ቀን ነው፣ የአለምን ሁኔታ ትተን በአገራችን ኢትዮጵያ ያሉ አካል ጉዳተኛች የሚደረግላቸው ድጋፍና እንክብካቤ
ምን ይመስላል? ወደሚለው ስናልፍ ደግሞ የሚያሳፍር ሆኖ እናገኘዋለን፣
ምክንያቱም እነዚህ በጀግነንት የተጎዱ አርበኞች ዛሬ ረዳት አጥተው በደረሰባቸው
የአካል ጉዳት ምክንያት እያፈሩ ይኖራሉ፣ ዛሬ ለአካል ጉዳተኞች ያለው ክፍት የስራ ቦታ ምንድ ነው ብንል እንኳ ጎደና ወጥተህ ጨርቅ
በማንጠፍ መለመን ብቻ ሆኗል፣
ይህንን የመለመን እድልም ቢሆን የሚያጡበት አጋጣሚዎች እንዳለም ተደጋግሞ እየታዬ ነው፣ ምክንያቱ የውጭ ዜጎች ስለሚመጡ በዚህ ከተማ ውስጥ መታየት
የለባችሁም ተብለው በጭነት መኪናዎች እየታፈሱ ወደ በረሃ የሚጣሉ አካል ጉዳተኞች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፣
የኢህአዴግ መሪዎች እነኝህ ስለ አገርና ስለ ህዝብ ብለው አካላቸው ያጡ
የጦር ጉዳተኞች መንከባከብ ያልቻሉ ለሌሎቹ በተለያዩ ምክንያቶች አካላቸውን
ያጡ ወገኖቻችን እንዴት አይነት አያያዝ እንደሚደረግላቸው ሁላችን
እንደምንታዘበው የሚያሳዝን ነው። እንደዚህ
አይነት አስከፊ ድርጊቶች አገር በመምራት ላይ ነኝ ከሚል ስርአት
የማትጠብቀው ሲሆን አካል ጉዳተኞችም ተጨማሪ የህልና ጠባሳና ጉዳት
በመጨመር እየቀጠለ ይገኛል፣
ይህ በህዝቦቹ ስቃይ እና ሰቆቛ ቁማር እየተጫወተ ያለው ስርአት አሁን ያለበት የስልጣን ኮረቻ ለመዉጣት የቻለው የጉዳተኞች አጥንት ደም መሳልል በመጠቀም ስርአቱ ስልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን
ተተጋሎና ደሙን አፍስሶ ወደ ስልጣን ላወጣው ህዝብና አካሉ የጎደለውን አርበኛ መለስ ብሎ
ችግሩን ሊፈታለት አልቻለም፣
አካል ጉዳቶኞች
ካላቸው ችግር ለመላቀቅና ተምረው በእውቀታቸው ሰርተው
እንዳይተዳደሩም እነኝህ በጣት የሚቆጠሩ የአካል ጉዳተኞች ትምህርት
ቤቶች በትላልቅ ከተሞች ብቻ ስለሚገኙ በሩቅ ገጠር የሚገኙ ጉዳተኛ ከዚህ ከተጠቀስው እድል እጅግ የራቁ ናቸው፣ በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ተቀጥረው የሚሰሩ አካል ጉዳተኞችም እጅግ ጥቂት
ሲሆኑ እነዚህም ቢሆኑም መብታቸው በሚያረጋግጥ መልክ ህንፃዎቹ ለዊልቸር እንዲስማሙ ታስበው ባለመገንባታቸው
የተነሳ በችግር ላይ ችግር ሆኖባቸዋል፣
ምክንያቱም መንግስት ህዝባዊና መንግስታዊ ስራዎችን ለማከናወን የሚገነባቸው ህንፃዎች
ለአካል ጉዳተኞች ግምት ወስጥ ያስገባ ባለ መሆኑ አካል
ጉዳተኞች ለችግር እየተጋለጡ ማየት የተለመደ ነው፣
ሌላው የገዥው የኢህአደግ ስርአት ሕገ መንግስት ከሚጠቅሳቸው ነጥቦች አንድ ብንወስድ “አንድ አካል ጉዳተኛ
ተበድያሎህ ካለ ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ የለውም። ለዚህ
ጉዳይ የሚከታተል የፍትህ ኣካል ማሰርጃ ከፈለገ ማሰራጃ ማቅረብ ያለበት
የበደለው አካል ነው፣"ይላል።
ቢሆንም በአሁኑ ሰአት በአገራችን አንድ የአካል ጉዳተኛ
በአስተዳደር ተበድያሎህ ካለ ማሰርጃ እንድያቀርብ ሰለሚታዘዝና ለማቅራብም ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ ማሰረጃ ለማሰባሰብ አቅም ሰለሚያጥረው
ተገድዶ ነገሩን የሚተወው ብዙ ነው፣
ለማጠቃለል። ያህ በስልጣን ላይ ያለው ገዥው ስርአት ለማስመሰል ለ23
አመታት ያህል የአካል ጉዳተኞች ቀን በማለት የአዞ እምባ እያነባ ቢያከብረውም
ከመዶስከር አልፎ ለጉዳተኞች የፈየደው አንዳችም ነገር የለም፣
በመሆኑም ይህ ባለፈው ህዳር 24/2008 ዓ/ም “ማካተት ወሳኝ ነው” በሚል መፈክርና መሪ ቃል ያከበረውን
የአካለ ጉዳቶኞች ቀን በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በችግር ላይ የሚገኙትን የአካል ጉዳቶኞች ወገኖቻችን እውነተኛ ሁኔታ የሚወክል አይደለም፣