Thursday, February 14, 2013

በሽረ እንዳስላሰ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በወረዳዋ ከሚገኙ የወጣት ማህበራት የተወከሉ 40 ወጣቶችን በመሰብሰብ በህብረተሰቡ ውስጥ እሚናፈሱ ወሬዎችን ለጽ/ቤቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ መመሪያ ሰጠ፣




የከተማዋ የስፖርትና ወጣቶች ጽ/ቤት በስብሰባው ባቀረበው አጀንዳ መሰረት በህብረተሰቡ ውስጥ የሚናፈሱ ወሬዎች በተለይም የህወሓትን መከፋፈል የሚመለከቱ ወሬዎችን በመከታተል ለጽ/ቤቱ ሪፖርት እንዲያቀርቡ በስብሰባው ለተገኙ ወጣቶች መመሪያ ሰጥቷል፣ ወጣቶቹ የተሰጣቸውን መመሪያ ከልብ ባይቀበሉትም ከሚሰሩበት የመንግስት መ/ቤት እንዳይፈናቀሉና ከስራቸው እንዳይባረሩ ሲሉ ብቻ በስብሰባው ተስማምተው መውጣታቸውን ለማወቅ ተችለዋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በከተማዋ ገበያን ለማረጋጋት በሚል በህዝብ ገንዘብ ተገዝቶ መንግስት የሚቀርበውን የምግብ ዘይት በአከባቢው ባለስልጣናት ለነጋዴዎች ተላልፎ ስለሚሽጥ በከተማዋ የምግብ ዘይት በመጥፋቱ ምክንያት የከተማዋ ኗሪ መቸገሩን ቷውቋል ፣