በደረሰን ዘገባ መሰረት የአላማጣ ከተማ ኗሪ ህዝብ አንድ በመሆን ቁጭራና መጥረብያ በመያዝ ቤቱን ለማፍረስ
ከመጡት የፌደራል ፖሊስ ጋር በመፋጠጥ ቤቱን ከመፍረስ መከላከሉን ቷውቋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ ዜጎችን ማፈንና ማሰር ስራየ ብሎ የተያያዘው የኢህአደግ ስርዓት ከ 70 በላይ የሚሆኑ
ነባር የህወሓት ታጋዮችንና ከመከላከያ ሰራዊት የተሰናበቱ ወገኖችን ከመንግስት ጋር ጎን መሰለፍ ሲገባችሁ ለምን ከህዝብ ጋር ወገናችሁ
በማለት በፖለቲካ በማሳበብ እስር ቤት ውስጥ በማስገባት እያሰቃያቸው መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል፣
በተመሳሳይ በደሴ ፤ በከምሴና ገርባ የሚገኙ በርከት ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ ቃሊቲ እየተወሰዱ
የተጠየቃችሁት እመኑ በሚል በዱላ እየተቀጠቀጡና በኤሌክትሪክ እየተሳቃዩ ይገኛሉ፣