በደረሰን ዘገባ መሰረት በመቆፈር ላይ ያለው አዲስ ምሽግ በአፍዴራ ስራፕ በተባለ ቦታ ሆኖ የክልሉ ልዩ
ሃይል በተቆፈረው ምሽግ እንዲሰፍር ተደርጓል፣
ልዩ ሃይሉ ተቋውሞ ሊያነሳሳ ይችላል በሚል ስጋት ከኬሩ ዞን ፤ ድድጋ ወረዳ ተነስቶ ምሽግ ውስጥ እንዲገባ
የተደረገ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል፣
በተመሳሳይ ከማእከላዊ እዝ ፤ 108ኛ ኮር ፤33ኛ ክ/ጦር 7ኛ ሬጅመንት 4ኛ ሃይል በጥቂት ቀናት ውስጥ
30 የስርዓቱ ወታደሮች መክዳታቸውን ቷውቋል፣
በ4ኛ ሃይል የሚገኙ ወታደሮች ክዳት ይፈጽማሉ በሚል ስጋት ከካምፕ እንዳይወጡ ቢደረግም ባገኙት አጋጣሚ
ሁሉ እየተጠቀሙ ወደ መረጡት አከባቢ በመጥፋት ላይ መሆናቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፣