Thursday, February 14, 2013

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት በተደረገው የተማሪዎች ተቃውሞ የዩኒቨርሲቲው ንብረት የሆኑ ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ቷውቋል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በዩኒቨርሲቲው የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ዲን የዶ/ር መብራህቱ ላንድ ኩሩዘር መኪናም በተማሪዎች በተደረገው ተቃውሞ መውደማቸውን ለማወቅ ተችለዋል፣
በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተነሳውን ተቃውሞ ከወዲሁ ለማፈንና ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ሽረ ከሚገኘው የማእከላዊ እዝ በርካታ ወታደሮችን በማስመጣት በሰላማዊ መንገድ ተቃውማቸውን ሲገልጹ በነበሩ ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሰዋል፣ ጉዳት ከደረሰባቸው ተማሪዎች መካከል በአክሱም በቅድስተ ማሪያም ሆስፒታል ገብተው በመታከም ላይ መሆናቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያረዳል፣
የተማሪዎችን ተቋውሞ ተከትሎ በዩኒቨርሲቲው የተከሰተው ውጥረት ስላልረገበ አሁንም በግቢው ያለመረጋጋት ይታያል፣