በደረሰን ዘገባ መሰረት ከጥር 24,2005 ዓ/ም ጀምሮ የፌደራል ፖሊስ ፤ የክልሉ የፖሊስ አባላትና የአከባቢው
ታጣቂ ሃይሎች ቤት ለቤት እየዞሩ የሎግያንና የሰመራን ህዝብ ከፍላጎቱ ውጭ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ ጫና ቢያደርጉም የአካባቢው
ህዝብ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ፣ የህዝቡ እምቢተኝነት ያሳሰባቸው በአከባቢው የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች ስጋታቸውን ለሚመለከትው
አካል በመግለጽ ላይ ናቸው፣
ይህ በእንዲህ እያለ የአፋር ክልል የጸጥታና ፍትህ ሃላፊ ስዩም አወል የተባለ ካድሬ በአፍዴራ ጨው በማምረት
ላይ የነበሩ ከ 250 ሽህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ፈቃዳቸውን በመቀማት በጥቅማ ጥቅምና በዝምድና ለሌሎች አሳልፎ በመስጠት ለዓመታት
ሲሰሩበት ከነበረው የስራ ቦታ እንዲባረሩ በማድረጉ በአከባቢው ውጥረት መስፈኑ ለማወቅ ተችሏል፣