Friday, March 22, 2013

በምእራብ ጎጃም ዞን ፤ በፍኖተ ሰላም ወረዳ ተመድበው በስራ ላይ የሚገኙ ዳኞችና የፖሊስ አባላት በጉቦና ጥቅማጥቅም በመስራትና ፍትህን በማዛባት ወንጀሎኞችን ነጻ ይለቃሉ፣




ነዋሪነታ በፍኖተ ሰላም ወረዳ የሆነች አንዲት ሴት ልጅን በመድፈሩ ክስ ተመስርቶበት በህግ ስር እንዲውል የተደረገ ወጣት አሳየ ኑሬ በወረዳዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሚሰሩ ሁለት ዳኞችና የፖሊስ አባላት ጉቦ በመስጠት ነጻ መውጣቱ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
በደረሰን ዘገባ መሰረት በከባድ ወንጀል ተከስሶ በህግ ስር የነበረው አሳየ ኑሬን የተከሰሰበትን ወንጀል በሚገባ አጣርተው ወደ እሚመለከተው አካል በማቅረብ ተገቢውን ፍትህ እንዲያገን ማድረግ ሲገባቸው የፖሊስ አባላት ከፍትህ ይልቅ የግል ጥቅማቸውን በማስቀደማቸው ከዳኞች ጋር በመመሳጠር ጉቦ በመቀበል ወንጀለኛውን ነጻ በመልቀቃቸው ተበዳይዋ ፤ የተበዳይዋ ቤተሰቦችና የአከባቢው ሴቶች ቡሁኔታው ማዘናቸው ቷውቋል፣
በመጨረሻም በወረዳዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፖሊስ አባላት የታየው ስልጣንህን አለአግባብ በመጠቀም ፍትህ አዛብቶ የራስን ጥቅም የማስቀደም ተግባር በወረዳዋ ብቻ የሚታይ ችግር ሳይሆን አገሪቱን እየመራ ያለ የኢህአዴግ ስርዓት የሚከተለው ብልሹ አሰራር ነጸብራቅ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ፣