1-ህዝቡ በአስተዳደሩ እምነት በማጣቱ ከመንግስት እየራቀ ነው፣ የፊታችን ሚያዝያ በሚደረገው ምርጫም ይሁን
በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የህዝብ ተነሳሽነት የለም ፣ በዚህ ረገድ በወረዳ ካቤነ የተሰራ ምን አለ?
2- ቀደም ሲል ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ሲቀሩና ሲያቋርጡ ነበር የሚታየው አሁን ግን መምህራን ካለፉት
ግዝያት በተለየ መልኩ ስራቸውን በፈቃዳቸው በመልቀቅ ላይ ናቸው ምክንያቱ ምንድን ነው?
3-መንግስት ባስቀመጠው የግብር አከፋፈል አሰራር ምክንያት ህዝቡ መንግስትን እየራቀው ነው፣ በዚህ ረገድ
ምን መደረግ አለበት?
4-ክትትልና ጸጥታ በሚመለከት በየቀኑ በሞባይልና በቤት ስልክ ወደ ባለስልጣናት እየደወሉ እሚሳደቡ ግለሰቦች
አሉ-እነዚህን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በዞን አስተዳዳሪው ለተሰብሳቢዎቹ ቀርበው የስብሰባው መነጋገሪያ
አጀንዳም የነበሩ ሲሆን በተጨማሪም
-በሽረ-እንዳስላሰ የሚገኝ ስሑል ሆስፒታል ብቁ ባለሞያዎች የመድሃኒት አቅርቦት የለም በመሆኑም የአከባቢው
ህዝብ መንግስት የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት በመተው በግል የህክምና ማእከላት የሚሰጠውን አገልግሎት ይመርጣል፣ ምክንያቱ ምንድን
ነው?
-በመላ
አገሪቱ ካሁን በፊት ያልታየ የሃይማኖት ግጭት እየተባባሰ በመሄድ ላይ ነው ፣ በዚህም ምክንያት የህዝቡ ንብረት እየወደመና ሰውም
እየታሰረና እየሞተ ነው፣ መንግስት ሁኔታውን ተቆጣጥሮ ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት እንዴት ተሳነው? የሚሉ ጥያቄዎችም በወረዳዎቹ የካብኔ
አባላት ቀርበው በስብሰባው ውይይት የተደረገባቸው ቢሆንም የስርዓቱን እድሜ ለማስቀጠል ከሚደረግ ሙከራ ውጭ ህዝብን የሚጠቅም አንዳችም
ፍሬ በስብሰባው እንዳልተነሳ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣