Friday, April 12, 2013

በመቐለ ከተማ በዓረና ትግራይ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች የተለያዩ ወከባ እየደረሳቸው እንዳለ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት አቶ ይኩኖ ገሰሰ የተባለ ኗሪነቱ በመቐለ ከተማ ፤ በዓይደር ክ/ከተማ የሆነ ቀደም ሲል የህወሓት ታጋይ የነበሩና በአሁኑ ግዜ የዓረና ትግራይ አባል በመሆኑ ብቻ በፖሊስ አባላትና በስርዓቱ ካድሬዎች የተለያዩ በደሎች እየደረሱበት ለማወቅ ተችሏል፣
      አቶ ይኩኖ በተደጋጋሚ ማታ ማታ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች እቤቱ ድረስ እየመጡ በህይወት መቆየት ትፈልጋለህ? መሰንበት ከመረጥክ አርፈህ ተቀመጥ እኛ የ 50 ዓመት መሰረት እየጣልን አንተ ከዓረና ጋር ተጠግተህ በ 5 ዓመት ውስጥ ስልጣን ለመያዝ የምታደርገው መሯሯጥ አቋርጥ በማለት እንዳስፈሯሩትና ያለ ምንም ምክንያትም ለ 20 ቀናት ግለሰቡን እስር ቤት ውስጥ በማስገባት ፍርድ ቤት ሳይቀርብ እንደለቀቁት የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣