Friday, April 12, 2013

በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን የሚገኙ ካድሬዎች ትህዴን የላካቸው ሰርጎ ገቦች ገብተዋል በሚል ሰበብ የአከባቢውን ህዝብ እያዋከቡት መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ በማይ ሓንሰና ሕንጻጸ የተባሉ አከባቢዎች ትህዴን ያሰማራቸው ሰርጎ ገቦች ትጥቃቸውን ደብቀው ገብተዋል በማለት የፌደራል ፖሊስና የሚሊሽያ ሃይል በአከባቢው በማሰማራት ቁጥራቸው 12 ሽህ የሚሆኑ በባህላዊ መንገድ ወርቅ በማምረት ላይ የነበሩ ወገኖችና የአከባቢው ኗሪዎችን ከመጋቢት 27/ 2005 ዓ/ም ጀምረው ጨለማን ተገን በማደረግና ሃይልን በመጠቀም ከአከባቢው እንዲነሱ ማደረጋቸውን ለማወቅ ተችለዋል፣
አምባገነኑ ስርዓት እንዲህ ዓይነቱን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ዋና ምክንያት ብቻውን ተወዳድሮ ብቻውን ለማሽነፍ እያደረገው ያለ መሯሯጥ ስጋት እየፈጠረበት ስለመጣ ከተለያዩ አከባቢዎች የመጡትን በባህላዊ መንገድ ወርቅ በማምረት ላይ የነበሩ ወገኖችን ወደየመጡበት አከባቢ እንዲሄዱ በማድረግ በየአከባቢው ወሬ እንዲናፈስና ህዝቡን ውጥረት ውስጥ በማስገባት የግድ እንዲደግፉት ለማድረግ ቢሆንም ህዝቡ የስርዓቱን ሴራ ቀድሞ ስለደረሰበት ተቋውመውን ከመግለጽ ወደ ኃላ አላለም፣