ምንጮቻችን የላኩት መረጃ እንዳመለከተው በኦሮሚያ ክልል ወሊሶ ከተማ ቀበሌ 07 የሚኖር ህዝብ መሬት የመንግስት
ስለሆነ ልቀቁ የሚል መመሪያ በማውረዳቸውና ነዋሪው ህዝብም ሃገራችንን ጥለን የትም አንሄድም በማለታቸው ምክንያት ነሃሴ 1 ቀን
2006 ዓ/ም ፖሊስ በህዝቡ ላይ በከፈተው ተኩስ 5 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 7 በከባድ መቁሰላቸውን ተገለፀ።
በከተማው ውስጥ የሚገኘው ነዋሪ ንፁሃን ወገኖቻችንን በግፍ የገደሉ የፖሊስ አባላት ወደ ፍርድ ይቅረቡ የሚል
አቤቱታ ወደ ሚመለከተው አካላት ባቀረቡበት ጊዜ ሰሚ ጆሮ ማገኘት ስላልቻሉ እስካሁን በከተማዋ በህዝብና በፖሊስ አባላት መካከል
ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኖ እንዳለ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።