Thursday, October 17, 2013

የኢህአዴግ መንግስት ህጻናትን ሳይቀር በውትድርና ሞያ ለመመልመል በመላ ሃገሪቱ ማስታወቅያ በማውጣት እየተንቀሳቀሰ ነው፣




በመላ ሃገሪቱ የተጀመረና መስከረም 30,2006 ዓ/ም የወጣ ማስታወቅያ ገና እድሜአቸው ለውትድርና ሞያ ያልደረሰ ከ 14-16 የእድሜ ክልል የሚገኙ ህጻናትን ጨምሮ ለመመልመል የሚያስችል በመሆኑ በመላ ሃገሪቱ ከህዝባዊ ተቃውሞ ገጥሞታል፣
በአማራ ክልል በባህርዳር በደብረማርቆስ ከተማ ከ 10ኛ እና 12ኛ ክፍልን አጠናቀው ነጥብ ያልመጣላቸው ተማሪዎችን ወደ ውትድርና ሞያ እንዲገቡ የስርዓቱ ካድሬዎች እየቀሰቀሱ ሲሆን በተለይም ተማሪዎችን ለማታለል እየተጠቀሙበት ያለው ዘዴ ወደ መከላከያ ስትገቡ በተለያየ ሞያ ትሰለጥናላችሁ የሚል የተለመደ ቅጥፈት መሆኑን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
በተማሪዎች በኩል ይህ ተግባራዊ የማይሆን የተለመደ የስርዓቱ ባህሪ ነው በማለት በተለይም በሶማልያ ሄዶ በማይመለከተው ጉዳይ ገብቶ እያለቀ ካለው ኢትዮጵያዊ ወታደር ትልቅ ትምህርት አግኝተናል በማለት እንደተቃወሙት ቷውቋል፣