Thursday, October 17, 2013

ኢህአዴግ መጭው የ 2007 ዓ/ም ምርጫን በማስመልከት የአ/አበባ ከተማ ኗሪዎችን ለማነጋገር ስብሰባ ጠራ፣




ስብሰባው ጥቅምት 1,2006 ዓ/ም የተደረገ ሲሆን አጀንዳውም በ 2007 ዓ/ም በሚደረገው ሃገራዊ አጠቃላይ ምርጫ ከአሁኑ ዝግጅት እያደረጉ እንዲቆዩ ሲሆን በተሰብሳቢዎች በኩል ምንም ዓይነት ዝግጅት እንደማይኖርና ይበጀናል የምንለውን ብቻ እንመርጣለን ሲሉ የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል፣
ተሰብሳቢዎቹ የኢህአዴግን ስርዓት የማህበራዊ አገልግሎት ፤ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፤ መብራትና የቴለ አገልግሎት የመሳሰልቱን ችግሮች ሳይቃለሉ በተለይም የኤለክትሪክ አገልግሎት ለጎረቤት ሃገሮች መሸጥ አግባብነት የለውም በማለት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል፣