Saturday, October 19, 2013

በመተማ ወረዳ ማንቲግ በተባለ ልዩ ቦታ የአራት ሰዎች ሬሳ አውላላ ሜዳ ላይ ወድቆ ተገኘ፣




ማንቲግ በተባለ ልዩ ቦታ የአራቱ ሰዎች ሬሳ ወድቆ ከተገኘ ብሁዋላ የአከባቢው መስተዳድር ሁኔታውን ለማጣራት በሚል ምክንያት ጥቅምት 4,2006 ዓ/ም የአከባቢው ኗሪዎችን ሰብስቧል፣ በስብሰባው የተገኙት ኗሪዎች ሰዎቹ የተገደሉት በአከባቢው በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ነው ሲሉ ተደምጠዋል ፣ ሃሳባቸውን በስብሰባው ከገለጹት በአከባቢው ታዋቂ ከሆኑ ሰዎች መካከል አቶ ገ/መድህን ዳኘው ይገኙበታል፣
ቀደም ሲል በዚሁ ወረዳ ሽኸዲ በተባለ ከተማ አንድ የፖሊስ አባል ወደ አከባቢው ስራ ፍለጋ በሄዱ ሁለት ዜጎች ላይ ጥይት ተኩሶ መግደሉን መዘገባችን የሚታወስ ነው፣