Saturday, October 19, 2013

የኢህአዴግ መንግስት ወጣቶችን ለውትድርና ሞያ ለመመልመል ሲያካሂደው የቆየ ፕሮፖጋንዳ ስላልተሳካለት በሃይል ማስገደድ ጀመረ፣




መንግስት በትግራይ ክልል ደረጃ ወጣቶችን በውትድርና ሞያ ለመመልመል ማስታወቂያ በማውጣትና የፕሮፓጋንዳ ስራዎችን በመስራት ለአንድ ወር ሙሉ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ቢሆንም በፍላጎቱ የሚመለመል ሰው አልተገኘም፣ በዚህም ከጥቅምት 6,2006 ዓ/ም ጀምሮ ወጣቶችን በመሰብሰብ ስራ የላችሁም በስርቆት ለመሰማራት ነው ወይ ፍላጎታችሁ? ሃሳባችሁ ምንድን ነው? በማለት ወጣቶችን በማስፈራራትና ጫና በማድረግ ላይ መሆናቸውን ቷውቋል፣
የክልሉ ባለስልጣናትና የመከላከያ ሰራዊት ሃላፊዎች በመቀናጀት በጋራ እያደረጉት ያለ እንቅስቃሴ በአንድ በኩል በስርዓቱ ብልሹ የትምህርት ፖሊሲ ምክንያት ነጥብ ያላገኙትን በሌላ በኩል ደግሞ ገና ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉትን ተማሪዎችን ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዲመለመሉ የሚገፋፉ ሲሆን በወጣቱ ዘንድ ግን ተቀባይነት ሳገኝ ቀርቷል፣
በመከላከያ ሰራዊት ያለውን የብሄረ ትግራይ ተዋጽኦ ከሚፈለገው በታች በመሆኑ ክፍተቱን ለመሸፈን ሲባል መከላከያ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን የሚታወቅ ነው፣