Friday, November 1, 2013

ቀደም ሲል ውህደት ለማድረግ ስምምነት ላይ የደረሱት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ት.ህ.ዴ.ንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ፍትህና እኩልነት ግንባር (ኢ.ህ.ፍ.እ.ግ) በሰራዊት ደረጃ ሙሉ ይፋዊ ውህደት አደረጉ፣





የኢህዴግን ስርዓት በመቋወም የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ካሉት የፖለቲካ ድርጅቶች መከካል እንዲህ አይነቱ ሙሉ ውህደት ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ሁለቱም ድርጅቶች ለፍትህና እኩልነት የሚታገሉና መሰረታዊ የዓላማ ልዩነት ያልነበራቸው ከመሆናቸውም በላይ ባለፉት ዓመታት በጋራ የተለያዩ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በጋራ መስዋእትነት እየከፈሉ የመጡ ናቸው፣
ውህደቱ በተፈጸመበት ወቅት የዓወት ንውጻዓት የባህል ቡድን በቦታው ተገኝቶ ውህደቱን የሚመለከቱና የሃገራችን ብሄር ብሄረሰቦች የሚገልጹ የተለያዩ ዜማዎች ፤ ድራማዎች ፤ ግጥሞችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ትሪኢቶችን በማቅረብ ዝግጅቶቱን ከፍተኛ ድምቀት ሰጥቶታል፣
የሁለቱን ድርጅቶች ሰራዊት አባላት በተፈጠረው ውህደት እጅግ የተደሰቱ ሲሆን ውህደቱ በተናጠል የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ለሚገኙት የተቃዋሚ ድርጅቶች ሁሉ በአብነት ሊወሰድ የሚችል መሆኑ ጠቅሰው ሁሉም ተቋዋሚዎች በአንድ ዓላማ ጥላ ስር ተሰባስበው ለአንዲት ኢትዮጵያ በመታገል የኢህ አዴግን ስርዓት በመቋወም የሚደረገውን ትግል ለማፋጠን ተመሳሳይ እርምጃ እንዲሰውስዱ ጥሪ አቅርበዋል፣