Tuesday, December 24, 2013

በደቡብ ክልል ኢትዮጵያ ጉራ ፈርዳ ወረዳ ሲኖሩ የቆዩ ከ 5000 በላይ የአማራ ብሄር ተወላጆች ንብረታቸው ተወርሰው እንዲባረሩ መደረጉ ለማወቅ ተችለዋል።




በመረጃዉ መሰረት ለቡዙ አመታት የእርሻ መሬትና ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በህጋዊ መንገድ ተሰጥትዋቸው እስካሁን ሲኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች የሆኑ ዜጎቻችን፤ አንዳች የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖራቸው የአማራ ብሄር በመሆናቸው ብቻ፤ ከ5000 በላይ ኣባወራዎች ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዲወሰን በማድረግ፤ የነበራቸው ንብረትና ሃብት ተወርሰው እንደተባረሩ ታዉቀዋል።
እናቶች፤ ህፃናትና አዛዉንቶች የሚገኙባቸው ዕድሜ ልካቸው ይኖርበት ከነበሩ ጉራ-ፈርዳ ወረዳ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች የእለት ጉርሳቸው እንኳ ሳይዙ፤ በስርአቱ የፀጥታ ሃይሎች ከመኖርያ ቤታቸው እየተጎተቱ አሰቃቂ በሆነ መንገድ እንደ ተባረሩና በዚህም ሳብያ ተበዳዮቹ ካለመኖርያ ቤት ማሃል በረሃ ላይ ስለተጣሉ፣ ለበሽታና ለሞት እንደተጋለጡ ባለፈው የዜና መልእክታችን  መዘገባችን  ይታውሳል።
በተመሳሳይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የክልሉ ተወላጆች የሆኑ በስልጣን ላይ ባለው ገዢ መንግስት ተደራጅተው በክልሉ ሲኖሩ ለቆዩ የአማራ ብሄር ተወላጆች በመኖርያ ቤታቸው ይሁን በሚንቀሳቀሱበት ቦታ እየተከታተሉ እንደሚያንገላትዋቸውና ባለትዳር ለሆኑ ሴቶችም አስገድደው  እየደፈርዋቸው እንደሆነ ያስረዳው ይሀው መረጃ፣ በዚህ ምክንያትም እኝህ የአማራ ብሄር ተወላጆች ለሂወታቸው ዋስትና በማጣታቸው ሳይወዱ ከክልሉ  ይወጣሉ የሚል በስርአቱ የታቀደ ተንኮል መሆኑ ከአከባቢው የደረሰን መረጃ አስረድተዋል።