Tuesday, December 24, 2013

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ-ሰላም ከተማ የሚገኙ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት የቀበሌ ቤቶች እየሸጡ ወደ ግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል።




በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን የፍኖተ-ሰላም ከተማ ሃላፊ ኣለባቸው ላቀና የጽሕፈት ቤቱ ከንቲባ ባለሞያ አየሁ የተባሉት ከአንድ በንግድ አስመጪና ላኪነት የተሰማራ ነጋዴ በመስማማት 14 የሚሆኑ የቀበሌ ቤቶች በመሸጥ ወደ ግል ኪሳቸው እንዳስገቡት ለማወቅ ተችለዋል።
   ይህ በባለስልጣናቱ እየተደረገ ያለው ህጋዊነት ያላሟላ ቤቶች የመሸጥ ተግባር፣ የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋርዎች  ታሕሳስ 4 /2006 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ ለተፈፀምው ወንጀል በጭብጥ አስደግፈው ያቀረቡት ሃሳብ መነሻ በማድረግ፣ ስልጣናቸው ተጠቅመው የህዝብና የአገር ሃብት እየመዘበሩ የነበሩ ሰዎች። ፍኖተ ሰላም ከተማ በሚገኝ እስር ቤት ታስረው እንደሚገኙ ከከተማዋ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
 መረጃው አክሎ ሌሎች በቁጥጥር ስር ያልዋሉ የወንጀሉ ተካፋይ የሆኑ የወረዳዋ ሃላፊዎች መኖራቸው ቢገለፅም፣ ተገቢ ቅጣት ሳይሰጣቸው መፋታትና ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋዉረው እንዲሰሩ ማድረግ፤ የተለመደ የስርኣቱ ተግባር ስለሆነ፤ ሓቀና ፍትሕ ይኖራል ብለን አንጠብቅም ሲሉ የአካባቢው ነዋርዎች በምሬት እየተናገሩ መሆናቸው ምንጮቻችን ከቦታዉ በላኩልን መረጃ ለማውቅ ተችልዋል።