Monday, December 23, 2013

በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኙ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በሚል የተደራጁ ማህበራት፣ በስርዓቱ የተበላሸ አስተዳደር ተሰናክለው እንዳሉ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ፣




በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ ዞን ሸሬ እንዳስላሴ ከተማ ከተደራጁ 25 የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት፣ በዞኑ ባለው የተበላሸ ሃላፊነት የጎደለው አሰራር፣ የተደራጁበትን አለማ ማሳካት ባለመቻላቸው ብስራቸው ታቅፈው የሚገኙ አባላት ለከፋ ማህበራዊ ሂወት ተጋልጠው ምሬታቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ የችግሩ ሰለባ የሆኑትን ዋቢ በማድረግ ምንጮቻችን ከቦታው ገልፀዋል፣
    እነዚህ ማህበራት በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ በ01፤ 03፤ 04 እና  በሌሎች ቀበሌዎች እየተሰራ ያለው የኮብልስቶን ንጣፍ፣ የዉሃ ማስተላለፍያ ቦዮች ለሌሎች እየተሰጠ ለኛ ለምን አይሰጠንም አድልዎ እየተፈፀመ ነው በማለታቸው፣ እንድ ፀረ መንግስት ተቆጥረው፣ ለተደራጁባቸው 25 ማህበራት የገንዘብ ብድር በሚጠይቁበት ግዜ ለአንድ ማህበር 900ሽህ ብር ብቻ እንዲወስዱ ስለተፈቀደ፣ አባላቱ ለምን በኛ ላይ ሲደርስ ይቀንሳል በማለት ሌላ ተቃዉሞ እንድያነሱ የሚደረጋቸው ሁኔታ እንደተፈጠረ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስታወቀ፣
     በዚህ ዓመት በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ለጥቃቅንና አነስተኛ ፅህፈት ቤት ተብሎ ከ75 ሚልዮን ብር በላይ የተመደበ ቢሆንም፣ በጽሕፈት ቤቱ ባለው የተበላሸ አሰራር የተደራጁ ማህበራት ከሥራቸው እየተሰናከሉ በመሆናቸው፣ አባሎቻቸው እያጋጥማቸው ላለው መሰናክል መፍትሄ በማጣታቸው የመፍረስና የመበታተን አደጋ አንጃብቦባቸው እንዳሉ ምንጮቻችን ከከተማዋ አስገንዝበዋል፣