Thursday, December 26, 2013

መልካም አስተዳደር ለማስፈን። መልካም ተነሳሽነትና ትግል ያስፈልጋል፣


የኢትዮጵያ ህዝብ ከረጅም አመታት ጀምሮ። ባለፉት ገዢ መደቦችና አለንልህ በሚሉት አምባገነኖች የተነሳ። መልካም አስተዳደር የሚለው ቃል ከተራ አነጋገር አልፎ ተግባር ላይ ሲውል እንድም ቀን አይቶት አያቅም፣ 



ያለፈው ታሪክ እንደሚያስታውሰን ኢትዮጵያ አገራችን የረጅም ዘመናት ስልጣኔ እንደነበራት ቢያስቀጥም። ይህን ስልጣኔና እድገት እንዳለ ጠብቃ እንዳትሄድ እንደ ትልቅ እንቅፋት ሆኖ ወደ ኋላ እንድትቀር ያስቻላትና አሁንም በተጠናከረ መንገድ እየቀጠለ እንድሄድ ዋነኛው ምክንያት ሆኖ ያለው። የመልካም አስተዳደር እጦት መሆኑ የሚካድ አይደለም፣
     ያለፉ ገዢዎች ማለት የሃይለስላሴና የደርግ ስርአት ይከተሉት በነበረ የአገዛዝ ስልት። አጠቃላይ የአገራችን ህዝብ እንደ ህዝብ እንዴት ለስርአቱ ተገዥ ሆኖ ይቀጥል እንጂ። የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሰብኣዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ እንዲጠበቁ፤ ህዝቦች ያለምንም ልዩነት በአገራቸው ውስጥ በሰላም ሰርተው  እንዲነሩ፤ ብህግ ፊት በእኩልነት እንዲዳኙ፤ ሃሳባቸው በነፃነት እንዲገልፁና እንዲቃወሙ በሚቻልበት መንገድ የሚካሄድ አልነበረም፣
     ስለሆነም እነዚህ ፀረ ህዝብ ስርአቶች በህዝብ ላይ እያደረሱት በነበሩ መለኪያ ያልነበረው በደል። በህዝቡ የተባበረ ክንድ መሰረታቸው መፍረሱና መነቀሉ የግድ ስለነበረ። ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ በአካሄደው መራራ ትግልና ወደር የለሽ የሂወት መስዋእትነት። የገዢዎቹ ስርአት ሊንኮታኮት ችለዋል፣
     የሚገርመው ነገር እነዚህ ባለፍት ስርአቶች የትግል ዘመን ለራሳቸው እንደተራማጅ ሃይሎች ቆጥረው። በነበሩት ፀረ ህዝብ ሃይሎች ላይ ለረጅም አመታት ከጭቁኑ ህዝብ ጎን ሆነው እየታገሉ የነበሩ ግለሰቦች። ወደ ስልጣን ከወጡ በኋላ በባሰ መንገድ ወደ ፀረ ዲሞክራሲያዊ አመለካከት ሰምጠው። ሃገርና ህዝብን ለመጉዳት መብቃታቸ ነው፣
     በአሁኑ ግዜ በስልጣን ላይ ያሉ የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች በደርግ ስርአት ግዜ። በወቅቱ ለነበረው ወተሃደራዊ ስርአት በመቃወምና። ስልጣን ወደ ህዝብ ይሸጋገር የሚለውን ህዝባዊ መፈክር አንግበው። በህወሓት፤ ኢህዴን፤ ኦሆደድና ሌሎች በወቅቱ እየታገሉ የነበሩ ድርጅቶች ውስጥ ታቅፈው ሲታገሉ የነበሩ ግለሰቦች መሆናቸው ሁሉም የአገራችን ህዝቦች ያቃቸዋል፣ ለምን   የነበረው ሁኔታ ከተቀየረ በኋላና፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን የህዝብ ልጆች ሂወታቸው ከከፈሉና ማለቅያ የሌለው የሃገርና የህዝብ ንብረት ከወደመ በኋላ። አገርን ከጥፋት የሚያድን መንግስት ከመምጣት ፈንታ። በባሰ መልኩ አገርን የሚያጠፋና የሚያፈራርስ ስርአት የተተካው? ለምን ይሆን ለ23 አመታት ያህል በአገራችን ውስጥ መልካም አስተዳደር እንዲኖርና ለውጥ እንዲመጣ ያልቻለው ብለን ለማየት ከፈለግን። መልሱ ግላዊ የስልጣን ጥማት የነበራቸው ታጋዮች እንጂ። ስልጣንን ከአምባገነኖች ነጥቀው ወደ ህዝብ ለማስረከብ ፍላጎት ያለነበራቸው ድብቅ አላማ ይዘው ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች ናቸው የሚለውን ቃል የሚገልፃቸው ይሆናል፣
      በአገራችን ውስጥ ስለ መልካም አስተዳደርና አጠቃላይ ስለ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ባለው ነባራዊ ሁኔታ አስመልክቶ። መጨረሻ የሌላቸው ስብሰባዎችና ግምገማዎች እንደሚካሄዱ ስርአቱ በተለያዩ መገናኛ ሚድያዎች ነጋ ጠባ ይናገርለታል፣ በተቃራኒ ደግሞ ህዝቡ እውነተኛ ፍትህ ስላጣና መብቱ ስለተነፈገ። ምንም መፍትሄ በማያስመጣ ስብሰባና ግምገማ ተማርሮ። እትብቱን የተቀበረበት መንደሩን ትቶ በመሰደድ ምክንያት። ለከፍተኛ ችግርና ለውርደት የተጋለጠበት ወቅት ላይ ይገኛል፣ 

    በአገራችን ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታና ሃቅ ይህን እያለ። ለምንድነው ሆን ተብሎ የራስህን ህዝብ ለማታለልና ለማደናገር። በተግባር ለማይታይ የመልካም አስተዳደር ነጋሪት የሚጎሸመው፣
    ሃሰት ሲደጋገም ሃቅ ይመስላል እንደሚባለው። በአገራችን ውስጥ ስላለው እውነተኛ መረጃ ለማያውቁ አንዳንድ ወግኖች በስርአቱ ሚድያዎች  ሊያደናገሩ ይችሉ ይሆናል። የችግሩ ገፈጥ ቀማሽ የሆነ  ሰፊው ህዝብ ግን። መልካም አስተዳደር የሚረጋገጠው በትግል እንጂ በስብሰባና በግምገማ ጋጋታ ብቻ እንዳልሆነ ስለሚያውቅ። በስርአቱ ከሃቅ የራቀ ፕሮፖጋንዳ ፍፁም ሊደናገር አይቻልም፣