Thursday, December 26, 2013

በመቀሌ ከተማ አጋጥሞ ያለው የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረት መፍትሄ ባለማግኘቱ። ነዋሪው ህዝብ በተደጋጋሚ ብሶቱን እያሰማ መሆኑ ያገኘነው መረጃ እስታወቀ፣




     ሰሜናዊ ኮኮብ የሚል መጠርያ ይዛ የምትገኘውና በስርኣቱ የላቀ እድገት እንዳስመዘገበች የሚነገርላት የመቀሌ ከተማ። ነዋሪዎችዋ በንፁህ መጠጠ ውሃ እጥረት ሳብያ ለበርካታ አመታት እየተሰቃዩ መሆናቸው ቢታወቅም። ለችግሩ መፍትሄ የሚሰጥ የመንግስት አካል ባለመኖሩ። የነዋሪው ህብረተሰብ ሂወት ችግር ላይ መውደቁ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ፣
     የደረሰን መረጃ ጨምሮ እንደገፀው። በመቀሌ ከተማ አጋጥሞ ያለው የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረት አዲስ ክስተት ባይሆንም። በአሁኑ ወቅት ግን በከፋ ደረጃ ላይ እንዳለና። በተለይ ቀልቀል ደብሪ በመባል የሚታወቀው አካባቢ የሚኖር ህዝብ። የቧንቧ ውሃ ከማያገኝ ወራቶች በማስቆጠሩ። ሂወቱን ለማቆየት ሲል ጥራቱን ካልጠበቀ የውሃ ጉድጓድ እየተጠቀመና ይህንን ለማግኘትም ሰልፍ ይዞ እንደሚውል ያገኘነው መረጃ ገለፀ፣
    ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀልቀል-ደብሪ አካባቢ ነዋሪዎች። ኑሮኣቸው ለመምራት ትልቅ ማነቆ ሆኖ ላለው የውሃ እጥረት። መፍትሄ እንዲያገኙለት በማለት ህዳር 21/2006 አ/ም ወደ ሚመለከታቸው አካላት ቢያስታውቁም። ጥያቄያቸው ሰሚ ኣካል እንዳላገኘ መረጃው አክሎ ኣስረድተዋል፣