በአዊ ዞን፤ ጃዊ ወረዳ፤ ኣልኩራንድ ቀበሌ አልመሽ በተባለ ኣካባቢ በሚገኝ ህብር ስኳር ፋብሪካ ውስጥ በቀዋሚና
በጊዚያዊ ሥራ ላይ ተቀጥረው እየሰሩ ያሉ ከ1000ሺ በላይ ሰራተኞች። የአካባቢው አስተዳደር ሆን ብሎ ከሥራቸው ለማሰተጓጎልና ከፋብሪካው
አመራር ጋር አጋጭቶ የራሱን ወገኖች ለመተካት ካለው ፍላጎት የተነሳ። በዚህ ሳምንት በተከታታይ በሥራ ሰአት እንዲሰበሰቡ በማድረግና
በውስጣቹ አሸባሪዎች ሰርገው ገብተዋል በማማለት ራሳቹህ ማጋለጥ ይሻላቹሃል ብለን እንጂ። ከናንተ በፊት አውቀናቸዋል በማለት ሲያስፈራርዋቸው
እንደሰነበቱ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣
በደረሰን መረጃ መሰረት ሰራተኞቹን
በመሰብሰብና በውስጣቹህ ያሉ አሸባሪዎች አጋልጡዋቸው እያሉ እያስጨነቅዋቸውና ከሥራ ገበታቸው እያሰናከልዋቸው ከሚገኙ የስራአቱ ካድሬዎች
ውስጥ። የድርጅቱ የጽሕፈት ቤቱ ስራ እስከያጅ አይነ ኣዲስ፤ ስፐር ቫይዘሮቹ አቶ ነብርሸትና የቻለ ጋሹ፤ እንዲሁም የስራአቱ ፀጥታ
አስከባሪዎች የሆኑ ወተሃደር ካሳሁንና ወተሃደር ስንቴ በመሆን። ስልጣናቸው ተጠቅመው በሰራተኞቹ ላይ ውዥንብር በመፍጠር። እስካሁን
በርከት ላሉ ንፁሃን ወገኖች። የሰሩበትን ደመወዝ ሳይከፈላቸው እንዳባረርዋቸው ሊታወቅ ተችለዋል፣