Sunday, December 22, 2013

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቻችን መኖርያ ቤታቸው ስለ ፈረሰባቸውና ካለ መጠለያ ስለቀሩ። እስካሁን በረሃ ላይ ተጥለው እንዳሉ ከከተማው የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣



በደረሰን መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች የሚገኙ የነፋስ ስልክ፤ ላፍቶ፤ ሃናማርያምና ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሲኖሩ የቆዩ ከ 500ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች። ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በከተማዋ አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ በመፍረሱ ምክንያት። አብዛኛው ህፃናቶችና ሽማግሌዎች የሚገኙባቸው በርከት ያሉ ዜጎቻችን በረሃ ላይ ተጥለው። ለፀሃይ፤ ንፋስ፤ ውርጭና ዝናብ ለሕመምና ሞት እየተጋለጡ መሆናቸው ሊታወቅ ተችለዋል፣
     ይህ ታህሳስ 6/2006 አ.ም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅነት      በባለስልጣናት ትእዛዝ መሰረት ቤቶችን የማፍረስ ድርጊት። አያሌ ወገኖቻችን አደጋ ላይ እንዲወድቁ ያደረገ ተግባር መሆኑ የገለፀው ይህው መረጃ። ተፈናቃዮቹ በላያቸው የወረደው አሰቃቂ በደል አስመልክተው መፍትሄ እንዲሰጣቸው በማለት። በወኪሎቻቸው በኩል ለሚመለከተው አካል ጥያቄያቸው ቢያቀርቡም። ከህዝቡ ለተወከሉ ሰዎች ተቀብለው እንዳሰርዋቸው የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድተዋል፣
     መረጃው በመጨረሻ እንዳስታወቀው። ጥያቄያቸው ለማቅረብ ተልከው ከሄዱና በስርኣቱ ካድሬዎች ከታሰሩት ዜጎቻችን ውስጥ። ኣቶ ኑሩ ጀማል፤ ኣቶ ከድር ኣባተና ሌሎች ወገኖች እንደሚገኙ ተገልፀዋል፣