Tuesday, December 24, 2013

ህዝባዊና ሃገራዊ ሃላፍነት የሌላቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት የስልጣናቸው ዕድሜ ለማራዘም ሲሉ በክልልና በጎሳ የተደራጁ አካላት እያሰማሩ እናዳሉ ከምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።




የስርኣቱ  ጠቅላይ ሚስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ቀጣይ የስልጣኑ ዕድሜ ለማራዘም ሲል ብሌሎች ብሄር ተወላጆች ቁጥጥር ስር የቆየ የስልጣን ቦታ ቀስ በቀስ በደቡብ ክልል ተወላጆች እንዲተካ እያደረገ ምርቆየቱ የሚታወስ ሁኖ፤ አሁንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፐሬሽን ሃላፊ ለነበረው ለአቶ እሸቱ ከቦታው በማንሳት፤ ሰንደቁ ለተባለ የደቡብ ክልል ተወላጅ እንዲተካ ማድረጉ ታወቀ።
ይህ ለከፍተኛ የሥራ ቦታ የተሾመው ሰንደቁ የተባለ ባለፈው በደቡብ ክልል ኢትዮጵያ የድስትሪክት ሃላፊ የነበረ ሲሆን፣ ለሃለማርያም ደሳለኝ ቅርበት ያለውና የደቡብ ክልል ተወላጅ በመሆኑ ብቻ፣ እንደ አንድ ብቃት ያለው ሰዉ ተወስዶ፤ ለአቶ እሽቱ በማንሳት ከፍተኛ ሹመት ማግኘቱ በስርኣቱ ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ ጎጠኝነት የወለደዉ አለማግባባት እንደፈጠረና፣ በኮርፐሬሽኑ ዉስጥ ደቡብ እና ሰሜን በሚል ቡድን ተከፋፍለው በከፍተኛ ንትርክ ተጠምደው እንደሚገኙ ከስርኣቱ ዉስጥ ኣፈትልኮ ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።