በሃገራችን ውስጥ የነዳጅ ዋጋ እጅግ በጣም ጨምሮ ባለበት ግዜ በስልጣን የሚገኘው ገዢው ስርዓት ለተከሰተው
ችግር መፍትሄ እንደማብጀት በአንፃሩ በራሱ ቀጥጥር ስር የሚገኙ የነዳጅ ማከፋፈያ ተቋማት ከነበረው ዋጋ በእጥፍ ጨምረው እንዲሸጡ
በማድረግ፣ አሁን ያለው የነዳጅ ዋጋ ንረት ከእለት እለት እየጨመረ መፍትሄ ወደማይገኝለት ችግር እያመራ እንደሆነ የአዲስ አበባ
ነዋሪዎች አስገንዝበዋል።
በተለይ የአዲስ አበባ ነዋሪ ህብረተሰብ
በተደጋጋሚ እያጋጠመ ካለው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ጋር ተያይዞ። የነዳጅ ዋጋ ከእለት እለት በእጥፍ እጨመረ በመምጣቱ ዕለታዊ ኑሮአቸውን
መመራት ተስኖአቸው እንደሚገኙና የተከሰተውን ችግር ለሚመለከተው አካል አቅርበው እስካሁን ምንም አይነት መፍትሄ ማግኘት እንዳልቻሉ
ለነዋሪዎቹ መሰረት በማድረግ መረጃው አስረድተዋል።
በነዳጅ ዋጋ መጨመር የተነሳ በከተማዋ
ከቦታ ቦታ የሚመላለሱ አውቶብሶች፣ ከዚህ በፊት ከነበረው የአክፋፈል ታሪፍ እንዲጨምሩ ግድ ስለሆነባቸው፤ ነዋሪዎቹ ለአንዱ ችግር
መፍትሄ ሳያገኙ ሌላ ችግር እየተደራረበባቸው እጅግ በጣም ለከፋ ኑሮ ተጋልጠው እንዳሉ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድተዋል።