Tuesday, December 24, 2013

በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ የሚገኙ የግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊዎች በሙሱና ተዘፍቀው እንደሚገኙ ተገለፀ።




በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ የሚገኙ የግብርና ፅሕፈት ቤት ሃላፊዎች፣ ያልሰሩበት የህዳርና የጥቅምት የውሎ አበል እንዲሰራላቸው በማዘዝ የህዝብና የመንግስት ገንዘብ እያባከኑ እንደሚግኙ የጠቆሞው መረጃው፣ ይህን የህዝብ ገንዘብ እያባከኑ ከሚገኙ ሃላፊዎችም ግርማ ፈረደ የተባለ የጽሕህፈት ቤቱ ሃላፊ እንደሚገኝበት ለማወቅ ተችለዋል።
   ግርማ ፈረደ ስልጣኑ ተጠቅሞ ባንቡሉክ ከተባለ የቀጠና ማህበር 8 ኩንታል ማዳበርያ በመሸጥ፣ ለግል ጥቅሙ እንዳዋለውና የሸጠዉን መዳበርያ በተካሄደው ግምገማ ላይ የተነሳ ቢሆንም፣ የተወሰደበት አስተማሪ እርምጃ እንደሌለ ከወረዳው የደረሰን መረጃ ገልፀዋል።
መረጃው በመቀጠል ባላስልጣኑ በጽሕፈት ቤቱ ያሳያቸው የሙሱና ተግባር አስመልክተው ለገመገሙት የፅሕፈት ቤቱ ሰራተኞች ከተላያየ ጥቅማ ጥቅምና የትምህርት እድል እንዳስቀራቸው በተካሄደው ግምገማ ላይ ተበዳየቹ መግለፃቸው መረጃው አክሎ ኣስረድተዋል።