Sunday, December 29, 2013

የመቀሌ ነዋሪ ህዝብ በከፋ የማህበራዊ ችግር ውስጥ ባለበት ወቅት ከእምነቱና ፍላጎቱ ውጭ በሆነ መንገድ ለአካባቢው ልማት በሚል ሽፋን ገንዘብ እንዲያዋጣ እየተገደደ መሆኑ የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣




በመቀሌ ከተማ ውስጥ ሃወልቲ መስተዳድር አካባቢ የሚገኝ ነዋሪ ህብረተሰብ ባልተወያየበትና ባልወሰነበት መንገድ መስተዳድሩ ከ4.5 ሚልዮን ብር በላይ ለአካባቢው ልማት በሚል ሽፋን ለነዋሪዎቹ  ገንዘብ እንዲያዋጡ ትእዛዝ እንደሰጠና ለዚሁ ጥብቅ ትእዛዝ ተገዢ ሆኖ ያልተገኘና ፈቃደኛ ያልሆነ ማንኛውም አካል እንደ ፀረ መንግስትና ሃገር ተደርጎ ይወሰዳል በማለት፤ እስገድደው እንዲከፍል እያደረጉት መሆናቸው ሊታወቅ ተችለዋል፣
    ከከተማው ሳንወጣ ቀበሌ 16 እየተባለ በሚጠራ ቦታ በታህሳስ 18/2006 አ/ም ከሌሊቱ 4።00 ሰአት ላይ መነሻው ባልታወቀ ምክንያት ያጋጠመ ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ በርካታ ንብረት እንዳወደመ ምንጮቻችን ከቦታው አስታውቀዋል፣
     እንደ ምንጮቻችን ገለፃ የእሳት አደጋው ባጋጠመበት ሰአት። ነዋሪዎቹ ተባብረው ለማጥፋት ቢሞኩሩም። ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸው ከተማው ውስጥ ወደ ሚገኘው የእሳት አደጋ መከላከያ ድርጅት ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢያቀርቡም። ፈጣን ምላሽ ባለማግኘታቸው። ለውድመቱ አስከፊ እንዳደረገው መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣