በመረጃው መሰረት በሰሜን ምእራብ ትግራይ ዞን በሸራሮ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ከመከላከያ ሰራዊት የተሰናበቱ
ከፍተኛ ማእርግ የነበራቸው በርከት ያሉ መኮንኖች ንሮኣቸው ለመምራት ሲሉ በማህበር ተደራጅተው ህጋዊ ስራ በጀመሩበት ግዜ የስርኣቱ
የዞንና የወረዳው ኣስተዳዳሪዎች ሰንካላ የሆነ ምክንያት በመፍጠር እያሰርዋቸውና እያንገላትዋቸው መሆኑ ተገለፀ፣
እነዚህ ህጋዊ በሆነ መንገድ ማህበር
በማቛቛም ለራሳቸውና ላካባቢው ህዝብ በሚጠቅም ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የቀድሞ የህወሃት ታጋይ መኮንኖች የህወሃት ኢህኣዴግ
ባለስልጣኖች ካላቸው ውስጣዊ ያለመተማመን ተነስቶው፤ የትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱ ተቃዋሚዎች ትገናኛላቹህ በሚል ኡነትነት የሌለው ውንጀላ
በቅድምያ ሞራላቸው መሰበር ኣለበት ብሎው ላስቀመጥዋቸው (ኣርባዕተ ኣይኑ በመባል የሚታወቀው ኮረኔል ወ/ኣረጋይና) ሻለቓ ሙዘይ
ለተባሉ ግለሰቦች እስር ቤት ውስጥ ካስገብዋቸው በሃላ ቆይተው ያለ ምንም ፍርድ ኣስፈራርተው በዋስ መልቀቃቸው የገለፀው መረጃው
ኣሁንም በላያቸው ላይ ጥብቅ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ኣክሎ ኣስረድተዋል፣
ይህ በንዲህ እንዳለ ከሸራሮ ከተማ
ሳንወጣ የወያኔ ኢህኣዴግ ባለስልጣናት በያዝነው ሳምንት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ነጋዴዎች ኣስጠርተው ባካሄዱት ስብሰባ በነጋዴዎቹ
ጥያቄ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ከቦታው በተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችለዋል፣
ነጋዴዎቹ ካስነሱት ጥያቄዎች በጥቂቱ
ለግብርና ለልማት በሚል ምክንያት ከኣቅማችን በላይ ገንዘብ እየከፈልን ብንሆንም እስካሁን ድረስ በከተማው ውስጥ የሚገኝ የንፁህ
ወሃ እጥረትና ሌሎች ማህበራዊ ፍላጎቶች ሳይፈቱና የምንከፍለው ገንዘብ የት እየደረሰ መሆኑ ሳናውቅ፣ የመደራጀታችን ፋይዳ ምንድ
ነው? የምንደራጅ ከሆነም ሙሉ ነፃነት ባለው መንገድ መሆን ኣለበት በማለት በኣንድ ድምፅ ላስነሱት ጥያቄ ስብሰባውን ሊመሩ ተብለው
የተላኩት የስራኣቱ ካድሬዎች ኣናዳች መልስ ሳይሰጡበት ከመድረኩ ሸሽተው እንደሄዱ ለማወቅ ተችለዋል፣