Friday, January 17, 2014

በመቀሌ ከተማና ኣካባቢዋ ተመድበው ሲሰሩ የቆዩ የፖሊስ ኣባላት የስራ ስንብት ወረቀት እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ኣወንታዊ መልስ እንዳልተሰጣቸው የተገኘው መረጃ ኣስታወቀ፣




በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማና ኣካባቢው የሚገኙ ለወያኔ ኢህኣዴግ ስርኣት ሲያገለግሉ የቆዩ የፖሊስ ኣባላት በስራኣቱ ህገ ደንብ መሰረት ቀደም ሲል ከስራቸው ሊሰናበቱና ወደ ቤተሰባቸው ወደ ሚገኙበት ኣካባቢ ዝውውር ሲጠይቁ መብታቸው የተጠበቀ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፤ ባሁኑ ግዜ ግን ከስራው ለመውጣት ይሁን የዝውውር መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ለሚመለከታቸው ኣካላት በተደጋጋሚ ጥያቄያቸው ቢያቀርቡም እስካሁን ድረስ ተገቢ መልስ እንዳልተሰጣቸው ከቢሮው ውስጥ በደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችለዋል፣
      የፖሊስ ኣባላቱ ፀረ ህዝብና ብልሹ  ለሆነው ስራኣት እያገለገሉና ህዝብን እየበደሉ ንሮኣቸው መቀጠል ስላልፈለጉ ከስራው ለመሰናበት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ከ7 ኣመት በላይ ስላገለገልን የስንብት ወረቀት ይሰጠን ብለው ላቀረቡት ህጋዊ ኣቤቱታ ሰሚ ማግኘት እንዳልቻሉ ተገለፀ፣
      ስርኣቱ በውስጡ ያለው የፖሊስ እጥረት ለመሸፈን ኣዳዲስ የፖሊስ ኣባላት ለመቅጠር ላወጣው ተደጋጋሚ የቅጥር ማመልከቻ፤ ወጣቶቹ ወደ ፖሊስ ሊቀጠሩ ፈቃደኞች ባለመሆናቸውና ምናልባትም የተቀጠሩ ካሉም በእድሜ የገፉና እምብዛም ትምህርት የሌላቸው ስለሆኑ በውስጣቸው ላለው የስራ ክፍተት ለመሸፈንና ቀደም ሲል ከመስኩ ተሰናብተው ወደ ተቃዋሚዎች እየተሰለፉ ነው የሚል ጥርጣሬ ለማስቀረት ሲባል የስራ ስንብት ፍቃድ እንደተከለከለ መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣