Monday, March 10, 2014

በታህታይ ቆራሮ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች በነዋሪዎቹ ላይ ግፍ እያወረዱ መሆናቸው ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ ጣቢያ ለምለም፤ ቀበሌ አዲ-በዙት በተባለው አካባቢ የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ አስተዳዳሪዎች ለህዝብ የተሰጠው የእርሻ መሬት ነጥቀው እየወሰዱት መሆናቸውና ለተነጠቁት ወገኖችም ጥያቄ እንዳያስነሱ በማለት በቀበሌው ፈፃሚ አባል እያስፈራርዋቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል። 
    የስርአቱ ተላላኪ የሆነው የለምለም ቀበሌ የስራ አስፈፃሚ አካል ኣቶ አራፋይነ ተስፋይ ከሌሎች ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን ለነዋሪው ህዝብ እያስፈራሩና ይጠቀምበት የነበረ መሬት ያለ ምንም ካሳ እየነጠቁ ሃያ በሃያ በመባል ይታወቅ የነበረ መኖርያ ቤት በማፍረስ ተግባር እጅ እንደነበረው የገለፀው መረጃው በዚህ ተግባር የተቆጡ ወገኖችም ሊገድሉት አስበው ቦታው ድረስ ሄደው ሲያጡት በምትኩ ከ20 ሺ ብር በላይ የሚገመት ገለባ እናዳቃጠሉበትና በአካባቢው የሚገኙ የፀጥታና የፖሊስ አባላትም ይህን ድርጊት የፈፀመው ማን ነው አጋልጡት በማለት ነጋ ጠባ ስብሰባ እየጠሩ ህብረተሰቡን ፍዳውን እያሳዩት ቢሆኑም እስካሁን ግን የተገኘ ውጤት እንደሌለ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።