Wednesday, March 5, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሽሬ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች በኢህአዴግ ካድሬዎችና የፀጥታ አካላት የተለያዩ ግፎች እየወረደባቸው እንደሆነ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



እነዚህ በሽሬ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የስርአቱ ታጣቂዎችና ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ግፍ እየፈጸሙ እናዳሉና በደሉ ከደረሳቸው ማሃልም ወጣት ሃረጎት የተባለ እንደሚኝባቸው የገለፀው መረጃው ግለ ሰቡ ምንም ዓይነት ወንጀል ሳይፈፅም በየካቲት 7 2006 ዓ/ም በዱላ እየደበደቡ ወደ እስር ቤት እንደወሰዱት ተገለፀ።
    ወጣት ሃረጎት ተጨባጭነት በሌለው መንገድ በጥርጣሬ ተነሳስተው ለስድስት ዓመት እንዲታሰር የተፈረደበት ሲሆን ሽሬ ከተማ ወደ ሚገኘው እስር ቤት ከገባ በኋላም። በላዩ ላይ የከፋ ድብደባና ስቃይ ይደርስበት እንደነበረና ከስድት ወር በኋላ ከእስር ቤቱ ሸሽቶ እንዳመለጠ ለማወቅ ተችለዋል።
     ግለሰቡ በማምለጡ የተበሳጩ የእስር ቤቱ ሃላፊዎች በወቅቱ በጥበቃ ስራ ላይ የነበሩ በርሀና ወዲ ኩማ የተባሉ ሁለት የፖሊስ አባላት ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈፀመው ነው። ስለዚህ ወንጀለኛው ከየትም አምጥታቹህ አስረክቡን የሚል ጥብቅ ትእዛዝ ስለተሰጣቸው የመለጠው ታሳሪ  አድነው ለመያዝ ብፍለጋ ስራ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ መረጃው አክሎ ኣስረድተዋል።