Wednesday, March 5, 2014

የገደባትና የልጉዲ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጎኖቻችን በሱዳን ፖሊሶች ከቦታው እየተፈናቀሉ መሆናቸው ከአባቢው በተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።



እነዚህ በገደባትና ሉጉዲ በተባለው አካባቢ ለረጅም ዓመታት ሲኖሩ የቆዩ ወገኖቻችን በየካቲት 6/2006 ዓ/ም የሱዳን ፖሊሶች ድንበር ጥሰው ወደ አካባቢው በመግባት ቦታው የኢትዮጵያ መንግስት ስለሰጠን ይዞታችን ነው ልቀቁልን በማለት በሃይል አስገድደው እያፈናቀልዋቸው እንዳሉ ተገለፀ።
     የአገራችን ቦታ በመሆኑ በአካባቢው ለረጅም ዓመታት ሲኖሩ የቆዩ እነዚህ ወገኖች ዛሬ በሱዳን ፖሊሶች ተገደው ከአገራቸው መሬት ውጡ መባላቸው ስላልተቀበሉት መሬታችን አሳልፈን አንሰጥም በማለት ብሶታቸው ለሚመለከታቸው አካላት ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ እንዳላገኙ ለማወቅ ተችለዋል።
     እየተካሄደ ባለው የማፈናቀል ድርጊት ብዛት ያላቸው ህፃናትና ሽማግሌዎች የሚገኙባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች አውላላ በረሃ ላይ ተጥለው ለፀሃይና ለብርድ በመጋለጣቸው ምክንያት እየተሰቃዩ ናቸው ስል መረጃው አክሎ አስረድተዋል።