በመረጃው መሰረት የሸራሮ
ከተማ አስተዳዳሪዎች በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ባለሃብቶችና ነጋዴዎች በየካቲት 9/2006 ዓ/ም ሰብስበው ላይ ለምንድነው ግብር የማትከፍሉ
በማለት ቢገመግምዋቸውም በስብሰባው ወቅት የተገኙት ባለሃብቶችና ነጋዴዎች ግን ግብር መክፈል ግዴታችን መሆኑ ስለምናቅ በወቅቱ ከፍለን
ስናበቃ እንደገና እንድንከፍል እያስገደዳችሁን ነው በማለት ብሶታቸው በምሬት እንደገለፁ ለማወቅ ተችለዋል።
ነጋዴዎቹ በማስከተል ይህን ያቀረባችሁት ግምገማ ቅንነት የሌለውና ጉቦ
ባለመስጠታችን የምታመጡት ያለ ምክንያትና በግብር ስም ንብረታችንና ገንዘባችን ለመውረስ ስለፈለጋቹህ ነው ህዝቡን ሰብስባቹህ ጥፋተኞች ለማስመሰል የምትሞኩሩት በማለት ቅሬታቸው
እንደገለፁ መረጃው አመልክተዋል።
በወቅቱ የሚገባቸውን ግብር ክፍለው እያለ እንደገና ተጨማሪ ግብር እንዲከፍሉ
የተገደዱና የሃሰት ጥላሸት ቀብተው እንዲገመገሙ ከተደረጉት መካከል ለመጥቀስ ሸራሮ የሚገኘው የሸራተን ሆቴል ባለቤት የሆኑ አቶ
ተስፋየ መዝገቦ፤ የሸራሮ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ አቶ አያሌውና አቶ
ገብረሃዋርያ የተባሉ እነደሚገኙባቸው ታውቀዋል።