ምንጮቻችን ባደረስሉን
መረጃ መሰረት የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ አቶ አባይ ወልዱ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ባለሃብቶች በተለይም ለትግራይ ተወላጆች
በየካቲት 9/ 2006 ዓ/ም ለምን ትግራይ መጥታቹህ ኢንቨስት አታደርጉም ብሎ ብቀረበው የስብሰባ አጀንዳ ላይ ተሰብሳቢዎቹ ትግራይ
ላይ ባለው የተበላሸ የአስተዳደር ስርአት ምክንያት ሰርተህ መኖር አይቻልም ሲሉ ሃሳባቸው እንደገለፁ ለማውቅ ተችለዋል።
መረጃው በማስከተል በስብሰባው ላይ የተካፈሉት ባለሃብቶች በትግራይ ክልል
ውስጥ እየታየ ያለው የአስተዳደር ብሉሽነት፤ ሙሰኝነትና ወገናዊነት የተሞላበት አሰራር ከሌሎች ክልሎች የከፋ ነው ካሉ በኋላ አሁንም
በተወለድንበት አካባቢ ገንዘባችን አፍስሰን ለራሳችን፤ ለወገናችንና ለአገራችን ለመጥቀም ሁኔታው መስተካከል አለበት ብሎው እንደተናገሩ
ለማወቅ ተችለዋል።
በትግራይ ክልል ውስጥ እየተፈጸመ ባለው ብልሹ አስተዳደር የተነሳ በርከት
ያሉ ባለድርጅቶችና ነጋዴዎች ወገኖቻችን ለኪሳራና ለእዳ ተጋልጠው አገራቸው ጥለው ወደ ስደት እንዲያመሩ ግድ እንደሆነባቸው ይታወቃል።