Friday, March 7, 2014

የዓረና ተቃዋሚ ድርጅት በተለያዩ የትግራይ ዘኖች በመንቀሳቀስ የቅስቀሳ ስራ እንዲያደርግ ቢፈቀድለትም ት.ህ.ዴ.ን በበተነው ፓምፕሌት ሳብያ ግን እንዲቋረጥ ምክንያት እንደሆነ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።



የዓረና ተቃዋሚ ድርጅት በተለያዩ የትግራይ ዘኖች በመንቀሳቀስ የቅስቀሳ ስራ እንዲያደርግ ቢፈቀድለትም ት.ህ.ዴ.ን በበተነው ፓምፕሌት ሳብያ ግን እንዲቋረጥ ምክንያት እንደሆነ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
    በመረጃው መሰረት የዓረና ተቃዋሚ ድርጅት በትግራይ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች በመንቀሳቀስ ቅስቀሳ ለማድረግ እንዲፈቀድለት ለሚመለከታቸው አካላት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ለጥር 30ና የካትት 3 /2006 ዓ/ም ስብስባ እንዲያደርግ ፍቃድ ቢሰጠውም በኋላ ግን ቅስቀሳውን እንዳያካሄድ በህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣኖች  ትእዛዝ እንደተሰጠው ለማወቅ ተችለዋል።
    የተቃዋሚው ድርጅት አመራሮች ቅስቀሳው እንዳናካሂድ የተከለከልነው ለም ይሆን ብለው ለሚመለከታቸው አካላት ላቀረቡት ጥያቄ ከስርአቱ ባለስልጣኖች በት.ህ.ዴ.ን ድርጅት የተዘጋጀ ፓምፕሌት በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በመበተኑ ምክንያት ነው የሚል መልስ ቢሰጣቸውም የዓረና ድርጅት አመራሮች ግን ት.ህ.ዴ.ን በበተነው ፓምፕሌት እኛ መታገድ አልነበረንም ሲሉ ክስ በማቅረብ ላይ እንዳሉ መረጃው አስታውቀዋል።
    መረጃው በማስከተል ይህ በትህዴን የተበተነውን ፓምፕሌት በህዝቡ ላይ ትልቅ ተቀባይነትና የደስታ ስሜት መፍጠሩ እንደገለፀና በአንፃሩ የስራአቱ ካድሬዎች ከባድ ስጋት ላይ ወድቃቸው ለማወቅ ተችለዋል።