Friday, March 7, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን የሚገኙ የፖሊስ አዛዦች ትህዴን በላያችን ላይ አደጋ ሊያደርስ እየተዘጋጅ ስለሆነ ለመከላከሉ እንዘጋጅ በማለት በበታች ለሚገኙ ሃላፊዎች ስብሰባዎች እያደረጉላቸው መሆንን ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



የትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን የፖሊስ አዛዥ የሆነው ኮማንደር ገብረኪዳን ኪዳኑ / ወዲ ሸራሮ / የተባለው የስርአቱ ካድሬ በሸራሮ፤ አዲ ዳዕሮና ሽሬ ለሚገኙ የወረዳው ፖሊሶች፤ የፀጥታ፤ የሚልሻ ሃላፊዎችና ኮማንደሮች የካቲት 7/2006 ዓ/ም ሰብስቦ ድርጅታችንና መንግስታችን በትህዴን ጥቃት እንዳይደርሰው ጠንቅቀን መስራት ይገባናል በማለት ጥብቅ ትእዛዝ እንደሰጣቸው ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።
    መረጃው በማስከተል የዞኑ የፖሊስ አዛዥ መስዋእት ከፍለን ላመጣናት የካቲት 11 ዛሬ የትህዴን አባላት በውስጣቹህ ሰርገው በመግባት አደጋ ሊያደርሱ እየተዘጋጁ ናቸው ስለዚ ሁላችንም እንጠንቀቅ በማለት ሃይል የተሞላበት ጥብቅ ትእዛዝ እንደሰጣቸው ተገልፀዋል።
     ይህ በእንዲህ እንዳለ በስልጣን ላይ ያሉ የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ባለስልጣኖች በህዝቡ ላይ ተቀባይነት አጥተው ባሉበት ግዜ እንዲህ ብለው መናገራቸው ጭንቀት ውስጥ የመግባታቸው ምልክት ነው ሲሉ የድርጅቱ አባላት ሳይቀሩ ለተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት በማድረግ እንደ መነጋገርያ እየተጠቀሙበት መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድተዋል።