Friday, March 7, 2014

የዓረና ተቃዋሚ ድርጅት የበላይ አመራሮች ከሚያደርጉት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውጭ የግል ስራ በሚያከናውኑበት ሰዓት ጭምር በስርአቱ ተላላኪዎች በቴሌፎንና በአካል የማስፈራርያ ተግባር እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገለፀ።



በዚህ መሰረት የማስፈራርያ መልእክት ከደረሰባቸው የድርጅቱ የበላይ አመራር የሆነው አቶ ስልጣን ሕሸ የተባለው እንደሆነና ከዚህ በፊትም በሁመራ ከተማ ድርጅቱን ወክሎ ለህዝብ ቅስቀሳ ለማድረግ በሄደበት ወቅት የትጥቅ ትግል ከሚያካሂደው ትህዴን ጋር ትገናኛለህ በሚል መሰረት የሌለው ውንጀላ ሁመራ ከተማ ወስጥ ታስሮ እንደነበረ ይታውቃል።
    አቶ ስልጣን ህሸ ከስራ ባልደርቦቹ ጋር ህዝቡን ለመቀስቀስ ወደ ሁመራ ከተማ በሄደበት ወቅት የከተማው አስተዳደር በወቅቱ ይስተናገድበት ወደ ነበረው ገነት ሆቴል ድርስ በመሄድ ለብቻው በማግለል አንተ የት.ህ.ዴ.ን ተባባሪ ነህ በማለት እንዳስፈራውና ሌሎችም በሚያካሂደው የቅስቀሳ ሂደትም እያስቸገሩት እንደነበሩ ይታወሳል ያለው መረጃው በዚሁ ሰንካላ የስርአቱ አሉባልታ ስራውን በሚገባ ሳያከናውን ወደ ቦታው እንደተመለሰ ይታወቃል።
    በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የሚገኙ የዓረና አባላትና ደጋፊዎች የህወሃት ኢህአዴግ ስርአት በሚያሰማራቸው ተላላኪዎች በሚደርስባቸው የማስፈራርያ መልእክት እለታዊ ኑሮአቸውን እንዳያከናውኑ ጫና እየፈጥሩላቸው እንደሆኑና ለሂወታቸው ዋስትና አጥተው በከባድ ችግር ላይ ወድቀው እንዳሉ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።