Sunday, March 2, 2014

በቃፍታ ሁመራ ወረዳ ኬላ ልጉዲ በተባለው ቦታ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከየካቲት ወር መጀመርያ ጀምረው ቦታቸው ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ተገለፀ።



እነዚህ በትግራይ ምእራባዊ ዞን ወረዳ ቃፍታ ሁመራ ሉጉዲ በተባለው ቦታ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ ወገኖች በአሁኑ ግዜ በብዙ ድካምና ጥረት ያፈሩት ተንቀሳቃሽ ያልሆነው ድርጅታቸውና ንብረታቸው ያለምንም ካሳ ትተውት እንዲወጡ ትእዛዝ እንደ ተላለፈባቸው የገለፀው መረጃው የመፈናቀሉ ምክንያትም የኢህአዴግ አመራር ባለ-ስልጣናት አካባቢውን ለሱዳን መንግስት አሳልፈው ስለ ሰጡት ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች እንዳሉ ከአካባቢው የተገኘው መረጃ አስታውቀዋል።
    ተፈናቃይ ወገነቹ ኣብዛኛዎቹ ቀደም ሲል በሱዳን “ትዋባ” በሚባለው የገዳሪፍ ከተማ አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ የኢ.ድ.ዩ አባላት የነበሩ መሆናቸውና አሁን በላያቸው ላይ እየተፈፀመ ያለው የማፈናቀል ተግባርም ምናልባት ከሱ ጋር የተሳሰረ ሊሆን እንደሚችል የችግሩ ሰለባዎቹ ጥርጣሬያቸው በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል።