በአማራ ክልል አዊ ዞን
ጃዊ ወረዳ ውስጥ የሚኖር ህብረተሰብ ስልጣን ላይ ባለው የኢህአዴግ ስርአት አንድ ለአምስትና ሰባት ለሰላሳ በሚለው አደረጃጀት ላይ
ተካቶ የቤቱና የአካባቢው ጤና ሁኔታ መጠበቅ ያልቻለ ግለ ሰብ ቤቱን መታሸግ አለበት የሚል ትእዛዝ ስለ ተሰጠ በርከት ያሉ መኖሪያ
ቤቶች ተገቢ ባልሆነ አሰራር ታሽገው እንደሚገኙ መረጃው አስታውቀዋል።
ይህን የአካባቢ ጤና ለመጠበቅ በሚል እየተካሄደ ያለው ቅጥ ያጣ አደረጃጀት
ለስርአቱ ፖለቲካ ስራ ማስፈፀምያ ነው ያለው መረጃው በዚህ አደረጃጀት ላይ አንገባም ያለ ነዋሪ እንደ አንድ የልማቱ አደናቃፊ ታይቶ
ልዩ ክትትል እንደሚደረግለትና በሽታ ለመከላከል በሚል ሰንካላ ምክንያት አመካኝተው መኖሪያ ቤት መዝጋት ስርኣቱ የስለያ መዋቅሩን
ለማጠናከር እያከናወነው ያለ መሰሪ ተግባር ነው ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች እንደተናገሩ ለመረዳት ተችለዋል።
በዚሁ በቂ ምክንያት የሌለው አሰራር ከየካቲት 8/2006 ዓ/ም ጀምሮ
መኖሪያ ቤታቸው የታሸገባቸው ወገኖች መፍትሄ ለማግኘት ሲሉ ለወረዳው ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አለባቸው ብሶታቸው ቢያቀርቡም።
የማውቀው ነገር የለም የሚል መልስ ስለ ሰጣቸው ችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ተገልፀዋል።
ከወረዳው ሳንወጣ በተለያዩ የወረዳው ጽሕፈት ቤቶች እየሰሩ የቆዩ ሰራተኞች
በግምገማ ሰበብ በላያቸው ላይ እየተፈፀመ ያለው የድብብቆሽ የጥቃት ዘመቻ ተማርረው ስራቸው የለቀቁ በርካታ ሆነው ከነዚህም ወ/ሮ
ትግስት ግርማ ከእርሻ ልማት ጽሕፈት ቤት የህክምና ባለሙያ፤ አቶ ስመኘው ፋንታሁንና አቶ ቢረሳው ከእርሻ ልማት ጽሕፈት ቤት፤አቶ
አደም ከስቢል ሰርቪስና ሁለት በሞክሺ ቢረሳው በሚል ስም የሚጠሩ በግብርና ጽሕፈት ቤት ውስጥ በአደረጃጀት ስራ ላይ ተሰማርተው
ሲሰሩ የነበሩ እንደሚገኝባቸው መረጃው አክሎ አስረድተዋል።