Sunday, March 2, 2014

ጤናን አስመልክቶ ሽንዲ ከተማ ውስጥ በተካሄደው የስድስት ወር ግምገማ ላይ ወንበርማ ወረዳ በአገልግሎት አሰጣጥና በስራ አፈፃፀም ላይ ደካማ እንደነበረ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።



    በመረጃው መሰረት በምእራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳ ሽንዲ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የአስተዳደሩ ጽሕፈት ቤት አዳራሽ የተሰበሰቡ የጤና ባለሙያዎችና ሃላፊዎች ከየካቲት 12/2006 ዓ/ም ጀምረው በፕሮጀክት ማስፋፊያ አስተባባሪነት የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት በአካሄደው የስድስት ወር ግምገማ ከ19 የገጠር ኬላ ጣቢያዎች፤ አንድ የከተማ ጤና ኬላና ሌሎች አምስት ጤና ጣቢያዎች የመጡ ባለሙያዎች እየሰሩበት ያለ አገልግሎት ሰጪ የጤና ማእከል ባለው ችግር ምክንያት ደረጃቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ስለተገመገመና የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል ተብለው ከተቀመጡ አገልግሎት ሰጪ ህክምና ጣቢያዎች ደረጃቸው በመውረዱ ምክንያት ሃላፊዎቹ መጥፎ ስሜት ውስጥ እንዳሉና በአይነ ቁራኛ እየተያዩ እንዳሉ መረጃው አስታውቀዋል።
    ይህ በወንበርማ ወረዳ የጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሃሪ ዳኛቸው እየተመራ የተካሄደው የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ የወንበርማ ከተማ የጤና ጥበቃ ሃላፊ የሆነው አቶ ሰለሞን ከዞኑ ውስጥ ከሚገኙ 15 የወረዳው ጤና ጣቢያዎች 13 ደረጃ ላይ እንደተቀመጠና በአጠቃላይ በወረዳዋ ውስጥ የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች፤ ጤና ኬላዎች፤ በአጠቃላይ በስራ አፈፃፀምና አስተዳደራዊ አገልግሎት ደካማ እነደነበረ በመድረኩ ተሳታፊዎች ስለተመገመና በግምገማውም መሰረት የመበላለጥ ደረጃ በመገለፁ ምክንያት በመሃላቸው ትልቅ ያለመረዳዳት ችግር ተከስቶ እንዳለ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።