Thursday, March 20, 2014

በአዲስ አበባ ካሳንችስ ክፍለ ከተማ ውስጥ ኳስ ሜዳ እንዲሰራ ተብሎ ወጪ የተደረገ በሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ ስራ ላይ ባለመዋሉ ምክንያት ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



በመረጃው መሰረት በአዲስ አበባ ካሳንችስ ክፍለ ከተማ ውስጥ ለኳስ ሜዳ መስርያ ተብሎ ከአንድ አመት በፊት ወጪ የተደረገው 60 ሚልዮን ብር እስካሁን ስራውን እንዳልተጀመረ የገለጸው መረጃው አንዳንድ የአካባቢው ህብረተሰብ ስራው ያለመጀመሩ ምክንያት ለማወቅ በማለት ወደ ሚመለከታቸው የከተማዋ ባለስልጣናት ሄደው ቢጠይቁም ሊሰራም ላይሰራም ይችላል የሚል ቀልድ አዘል መልስ እነደሰጥዎቸው ለማወቅ ተችለዋል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ ውስጥ በ2004 ዓ/ም ግዙፍ ስታድዮም እንዲሰራ ተብሎ በጀት መመደቡ ቢታወቅም ስርአቱ ግን ይሰራል ከማለት ውጭ ተግባር ላይ ያሳየው እንቅስቃሴ ባለመኖሩ የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ በስርአቱ ላይ ያለው ጥላቻ በመግለፅ ላይ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስታወቀ።
   የህወሓት ኢህዴግ ባለ-ስልጣናት ህዝቡን ለማደናገርና ፖለቲካዊ ጥቅማቸው ለማስጠበቅ ብለው የሚናገሩት የተስፋ ቃል። የተለመደው አስመሳይ ተግባራቸው ነው ሲል የአዲስ አበባ ነዋሪው ህብረተሰብ መግለፁ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።