Saturday, April 5, 2014

የሸራሮ ከተማ ነዋሪዎች ከፍላጎታቸው ውጭ ለመለስ ፋውንዴሽን የሚውል ገንዘብ እንዲያዋጡ እየተገደዱ መሆናቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



      በመረጃው መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ከሽራሮ ከተማ ህዝብ ብቻ ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን የሚውል ገንዘብ 1.5 ሚልዮን ብር እንዲያዋጡ መወሰኑን የገለፀው መረጃው ይህን ተግባር ላይ ለማዋል እየተፘፘጡ ያሉ የበታች አስተዳዳሪዎች ለእያንዳዱ ሰው እንዲከፍል በማስጨነቅ ላይ እንደሆኑ ተገለፀ።
     ይህ በእንዲህ እንዳለ ለመለስ ፋውንዴሽን የሚሆን ገንዘብ ለመክፈል አቅም የለንም በማለት ነዋሪዎቹ አሉታዊ መልስ በሰጡበት ግዜ ነጋ ጠባ ምክንያት እየፈጠራችሁ ገንዘቡን እንድንከፍል በማስገደዳችሁ ምክንያት ማህበራዊ ኑሮአችን ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየፈጠረብን ስለሚገኝ የምናዋጣው ገንዘብ የለንም በማለት ተቃውሟቸውን እንዳሰሙ መረጃው ገልጸዋል።
     በመጨረሻ ነዋሪዎቹ ይህ ህዝቡን እያታለልችሁ የምትሰበስቡት ገንዘብ ለህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለግል ጥቅማችሁ እያዋላችሁት መቆየታችሁን ህዝቡ በሚገባ ያውቀዋል አሁንም ለአንድ ግለሰብ ይህን ያህል ገንዘብ አዋጡ ብላችሁ ማስገደዳችሁ ሃላፊነት የጎደለው አስራራችሁን የሚያሳይ ነው ሲሉ በስርአቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ እንደገለፁ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።