Saturday, April 5, 2014

የማይ ካድራ ከተማ ነዋሪዎች በንጹህ ውሃ እጥረት ምክንያት እለታዊ ኑሮአቸውን መምራት እንደተሳናቸውና በዚህም የተነሳም ምሬታቸውን እያሰሙ መሆናቸው ከአካባቢው በተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችለዋል።

የማይ ካድራ ከተማ ነዋሪዎች በንጹህ ውሃ እጥረት ምክንያት እለታዊ ኑሮአቸውን መምራት እንደተሳናቸውና በዚህም የተነሳም ምሬታቸውን እያሰሙ መሆናቸው ከአካባቢው በተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችለዋል።
    እነዚህ በትግራይ ምእራባዊ ዞን ማይ ካድራ በተባለው ቦታ የሚገኙ ነዋሪዎች መንግስት ቃል የገባላቸውን የመሰረተ ልማት እጥረት መፍትሄ እንዲያደርግላቸው ለአመታት ጠይቀው ውጤት ማግኘት እንዳልቻሉ የገለፀው መረጃው ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ችግሩን ለመፍታት ብሎ ገንዘብ ቢያሰባስብም የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ተቀብሎው እንዳጠፋፉት ለማወቅ ተችለዋል።
    መረጃው በማስከተል ነዋሪዎቹ ጥራቱ ላልጠበቀ አንድ ጀሪካን ውሃ በ 6 ብር ሂሳብ ገዝተው እንዲጠቀሙ መገደዳቸውና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህፃናት የሚገኙባቸው የከተማ ነዋሪዎች በውሃ ወለድ በሽታዎች በመጠቃታቸው ምክንያት በስርአቱ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውና ተቃውሞ ካሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎችም አቶ ፍስሃ ወልደስላሴና አቶ ጋይም የተባሉ እንደሚገኙባቸው መረጃው አስታውቀዋል።