Saturday, April 5, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሑመራ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ለስፖርት ማጠናከርያ እየተባለ ከህዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብ በግላዊ ጥቅማቸው ላይ እያዋሉት መሆናቸው ተገለፀ።



ይህ ለስፖርት ትጥቅ መግዥያ እየተባለ ከህዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ የሁመራ ከተማ የወጣቶች እና ስፖርት ማህበር ጉዳይ ሃላፊ የሆነው አቶ ጎይተኦም ጉኡሽ ከግዢ ክፍል ሃላፊው በመሆን እንዳጣፋፉት ያወቁት ነዋሪዎች በህጋዊ መንገድ መፍትሔ እንዲደረግለት በየካቲት 13/2006 ዓ.ም ወደ ሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ብሶታቸውን ቢያቀርቡም የከተማዋ የፍትህ ጉዳይ ሃላፊዎች ግን ለነዚህ የህዝብ ገንዘብ ያጠፋፉ ግለ ስዎች ምንም አይነት እርምጃ እንዳልወሰዱላቸው ለማውቅ ተችለዋል።
   ይህ በእንድህ እያለ የከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ ወጪ አድርገውና ጉልበታቸውን አፍስሰው በማልማት ለአመታት ሲሰሩበት ከቆዩ የእርሻ መሬታቸው ለማፈናቀል በማሰብ 20 ሄክታር የያዘ ባለ ሃብት ኢንቨስተር ነው የሚል ቅንነት የጎደለው መምርያ በማውጣት መሬታቸው እየቀምዋቸዉ መሆኑን የጠቆመው መረጃው 10 ሄክታር መሬት ለያዘም 5 ይበቀሃል እያሉ እየቀሙት መሆናቸውና በዚህም ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ  በዚሁ ፍትሃዊነት የጎደለው አሰራር ተቃዉሞዉን እያሰማ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችለዋል።
   በተመሳሳይ በሁመራ ሲካሄድ በሰነበተ ስብሰባ ላይ በከተማዋ አስተዳዳሪዎች 20 ሄክታር ያላቸዉ ባለ ሃብቶች ወደ ኢንቨስተርነት እንዲሸጋገሩና ይህ ለማድርግ ደግሞ 400 ሺ ብር በባንክ ቤት ማስያዝ እንዳለባቸው ካልሆነ ግን መሬታቸው እንደሚነጠቁ የሚገልፅ መመርያ መፅደቁ ባለፈው የዜና እወጃችን ላይ መግለፃችን ይታወሳል።