Saturday, April 5, 2014

በሑመራ ከተማ ውስጥ ሰርተው ኑሮአቸውን ለመምራት ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ለመጡ ወገኖች በራሳቸውና በንብረታቸው ላይ በደል እየተፈፀመ መሆኑ ተገለፀ።



በሑመራ ከተማ ውስጥ ሰርተው ኑሮአቸውን ለመምራት ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ለመጡ ወገኖች በራሳቸውና በንብረታቸው ላይ በደል እየተፈፀመ መሆኑ ተገለፀ።
     እነዚህ ከመደባይ ዛና ወረዳ ነፋሲት ከተባለው አካባቢ ያላቸውን የኑሮ ችግር ለመፍታት ብለው ወደ ሁመራ ከተማ የመጡ ወገኖች በጉልበታቸውና በጋማ ጭነት እየታገዙ ከእርሻ መሬት ገለባ በማመላለስ ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ ቢሆንም እንደተለመደው በመጋቢት 10/2006 ዓ/ም ከሑመራ ከተማ ወጥተው ወደ እርሻ ቦታ ሲሄዱ ሑመራ አካባቢ የሚገኙ የጉምርክ ሰራተኞች የኮንትሮባድ አመላላሾች ናችሁ በሚል አሉባልታ የያዙዋቸውን ግመሎች ነጥቆው በመውሰድ አጫርቶው እንደሸጡዋቸው የደረሰንን መረጃ አስታወቀ።
     እነዚህ በህጋዊ መንገድ እየሰሩ እያሉ በኮንትረባንድ ምክንያት ግመሎቻቸው ተነጥቆ የተወሰደባቸው አካላት፣-
-    ከአቶ ተከስተ ገብረ 1 ግመል
-    ከኣቶ አፈወርቅ አስመላሽ 2 ግመል  
-    ከአቶ ገ/እዝጊአብሄር ሃጎስ 1 ግመል ተወስዶው በስርአቱ ተላላኪዎች በጨረታ እንዲሸጡ የተደረጉ ናቸው።
በግምሩክ ጥበቃ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የፀጥታ አባላት በኮንትረባንድ ምክንያት ተይዘው ከተሸጡ ንብረቶች ገቢ ስለሚያገኙ ባካባቢው ላይ በትሽከርካሪና ግመል ተጠቅመው ለሚሰሩ ንፁሃን ወገኖች ባልዋሉበት ጉዳይ የውንጀላ ጥላሸት በመቀባት በርከት ያሉ ንብረቶች በመንጠቅና ጉቦ በመቀበል የማይገባቸውን ገቢ በመሰብሰብ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ከቦታው በተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።