Wednesday, June 4, 2014

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የሚገኘው ዩኒቨርስቲ በአስተዳዳሪዎች ሆነ ተብሎ ግንቦት 16 2006 ዓ/ም እንደተቃጠለና በርካታ ንብረት እንደወደመ ተገለፀ።



ይህ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የሚገኝ ዩንቨርስቲ በክልሉ ባለስልጣኖችና በዩንቨርስቲው ሃላፊዎች በእሳት መቃጠሉን የገለፀው መረጃው ይህንን እኩይ ተግባር ሊፈፅሙ የቻሉት ደግሞ ለድርጅቱ ተብሎ የተበጀተ ገንዘብ ሂሳብ እንዳይወራረድ እና ጉዳያቸው እንዳይወጣ ስለፈሩ መዝገቦችንና ሰነዶችን ለማጥፋት ሆነ ብለው የፈፀሙት ውድመት መሆኑን መረጃው አስረድቷል።
     የእሳት ቃጠሎው በዩንቨርስቲው ውስጥ የነበረ በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ንብረት እንዲሁም  የተማሪዎች‘ና የመምህራን መኝታ ክፍሎች በመውደሙ ምክንያት። የዩንቨርስቲው ተማሪዎችና መምህራን ማረፊያ ቦታ በማጣታቸው በከፍተኛ ችግር እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
  የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት ተማሪዎችንና የአካባቢውን ህዝብ  በመሰብሰብ የእሳት ቃጠሎውን ያስነሱት የተቃዋሚ ድርጅቶች ናቸው በማለት የሃሰት ውንጀላ ብያቀርቡም  የአካባቢው ህዝብና የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ግን እውነታው ራሳቸው ባለስጣናት እዳይወጣ የፈፀሙት ወንጀል መሆኑን ስለተረዱት የሃሰት ውንጀላውን ሊቀበሏቸው እንዳልቻሉ ታውቋል።  
   ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ ጥፋት በፊት የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ የህዝብ ገንዘብ እየተጠፋፋ ነው በማለት ገንዘብ ያጠፋፉትን ባለሰልጣኖች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ክስ አቅርበው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።