Wednesday, June 4, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች የግንቦት 20ን በዓል አናከብርም በማለት አድማ ስላደረጉ በፌደራል ፖሊስ ተገደው በዓሉን እንዲያከብሩ እንደተደረገ ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታውቁ።



በመረጃው መሰረት የግንቦት 20ን በዓል በክልል ደረጃ ግንቦት 19 ሁመራ ከተማ የተከበረ ሲሆን የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ግን በዓሉ ወደ ሚከበርበት ቦታ አንሄድም በማለት አድማ ስላደረጉ የስርዓቱ ካድሬዎች የፌደራል ፖሊስ በቦታው በማሰማራት በከተማዋ የሚንቀሳቀሱትን ተሽከርካሪዎች እንዲቆሙ በማድረግ ህዝቡን አግተው በዓሉ ወደ ሚከበርበት ቦታ ሳይወድ በግድ እንዲሄድ እንዳደረጉት ምንጮቻችን ገለፁ።
   በባዕሉ ላይ የተገኙ ከፍተኛ የህወሃት ባለስልጣናት የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አባይ ወልዱና ምክትሉ ኪሮስ ቢተው፤ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ጎበዛይ ወልደአረጋይ፤ የስቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ ትርፉ ኪዳነ፤ የፖሊስ አዛዦችና የመከላከያ መኮነኖች የተገኙ ሲሆን ግንቦት 20ን ደግሞ ወደ ደጀና፤ ዳንሻና ሌሎች አካባቢዎች በመዘዋወር በልማት ስም እያወደሱ ህዝቡ ከስርአቱ  ለምን እንደራቀ በማነሳሳት የአዞ እንባ እያነቡ እንደሰነበቱ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።