Thursday, June 19, 2014

የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት አመራሮች ህዝቡ በሃገሩ ውስጥ ተንቀሳቅሶ እለታዊ ህይወቱን እንዳይመራ እየከለከሉት መሆናቸው ታወቀ።



ስልጣን ላይ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች የትግራይ ህዝብ በፈለገው አካባቢና ቦታ ሰርቶ ኑሮውን እንዳይለውጥ፤ በተለይ በተምቤን  አግበ በተባለ አካባቢ የጥበቃ ኬላዎችን በመክፈት ከዞን ወደ ዞን ሲንቀሳቀስ ለተገኘ ሰው የማንነት ወረቀት እንዲያሳይ ይህንን ማድረግ ላልቻለ ግለሰብ ግን እንደ ወንጀለኛ ታይቶ እንዲታሰር እያደረጉ መሆናቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ገለፀ።
     መረጃው በማስከተል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ  የማንነት ወረቀት ማግኘት መብቱ ቢሆንም በአሁኑ ግዜ ግን በትግራይ ክልል የማንነት ወረቀት እንዲሰጠው ለጠየቀ ነዋሪ መጀመርያ የህወሃት አባል መሆኑን የሚያረጋግጥ ምስክር ማቅረብ እንዳለበት። ካልሆነ ግን እንደማይሰጠው ለማወቅ ተችሏል።
     ይህ የተለመደ አሰራር መጪው ዓመት 2007 ዓ/ም የሚካሄደውን የይስሙላ ምርጫ ግምት ውስጥ በማስገባት ህዝቡን አስገድደው የህወሃት አባል ለማድረግ እንደሆነ የገለፀው መረጃው አባል አልሆንም ብሎ ለተቃወመና የተቃዋሚ ድርጅት ሆኖ እየሰራ ላለው ግን ተከፍተው ባሉት የጥበቃ ኬላዎች ላይ ይዘው እያሰሩትና ሰርቶ እለታዊ ኑሮውን እንዳይመራ እያደረጉት መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።