Sunday, August 17, 2014

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን መደባይ ዛና ወረዳ የገበያ ጉዳይ አጥኚ ክፍል ሆኖ ይሰራ የነበረ ግለሰብ 30 ሺህ ብር ይዞ እንደተሰወረ ታውቋል።



የምንጮቻችን መረጃ እንደሚያመለክተው በሰሜናዊ ምዕራብ  ዞን መደባይ ዛና ወረዳ የወረዳው የገበያ ጉዳይ ክፍል ሆኖ ይሰራ የነበረ ተስፋይ ብርሃነ የተባለ ግለሰብ ሃምሌ 29/ 2006 ዓ/ም ንብረት ለመግዛት ወደ መቐለ እንደተላከ 30 ሺህ ብር ይዞ እንደተሰወረ መረጃው አስረድቷል።
   የወረዳው አስተዳዳሪ ለሆነ  የመንግስታዊ ንብረት ግዥ የሚሄድ ሰው በግሉ ገንዘብ አስይዞ እንደማይላክ እያወቀ ከላከ በኋላ ለይምሰል ለዚህ ለጠፋው ሰራተኛ ያገኘ ሰው ገንዘብ እንሰጠዋለን የሚል የውሸት ማታለያ ወሬ እየነዙ እንዳሉ መረጃው አስረድቷል።
   በተመሳሳይ ከዚህ ዞን ሳንወጣ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኙ አንዳንድ የማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች የፅህፈት ቤቱን  ንብረት በሌሊት እያወጡ እየሸጡ መሆናቸውን ታውቋል።
   ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ  እንደሚያመለክተው በፅሕፈት ቤቱ የሚገኙ እንደ ኮምፒውተር፤ ቴሌቭዥንና ሌሎችም ተዛማጅ የሆኑ መገልገያ መሳርያዎችን እያወጡ እየሸጧቸው መሆናቸውን በመግለፅ መዘጋጃ ቤቱ ዘበኛ ቢኖረውም እንኳን እነዚህ የህዝብን ንብረት ለመውረር ነቅለው የተነሱ ሰራተኞች የማዘጋጃ ቤቱን ዘበኛ ወደ ሌላ ቦታ እንዲንቀሳቀስ በማድረግ በማዘጋጃ ቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት በመኪና ጭነው እያወጡት መሆናቸውን ለማወቅ ትችሏል።